ሳልሳይ ወያኔ «ሕገ መንግሥት ለማሻሻል እታገላለሁ»
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 29 2012ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ ለማድረግ እንደሚታገል ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ዐስታወቀ። በቅርቡ በትግራይ ከተመሰረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) አመራሩን መርጦ ፕሮግራሙንም ያጸደቀው ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ ባደረገው የመጀመሪያ ድርጅታዊ ጉባኤው ነው። የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ ኃያሉ ጎደፋይ ድርጅታቸው የትግራይን ጥቅም መሰረት ያደረገ ትግል እንደሚያደርግም መቀሌ ባሎኒ ሆቴል ውስጥ ሰኞ ማታ በሰጡት መግለጫ ገልጠዋል። ከዚህ በተጨማሪም ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የኢትዮጵያ ሕገ- መንግሥት ጠንካራ ክልሎችን በሚፈጥር ሁኔታ እንዲሻሻል ለማድረግ እንደሚታገል ሊቀ መንበሩ ተናግረዋል፡፡ ዝርዝሩን ሚሊዮን ኃይለሥላሴ ከመቀሌ ልኮልናል።
ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ