ሶማሊያ፤ ዓመጹና የፕሬዚደንቱ ሥልጣን መልቀቅ20 ታኅሣሥ 2001ሰኞ፣ ታኅሣሥ 20 2001የሶማሊያ ሽግግር መንግሥት ፕሬዚደንት አብዱላሂ ዩሱፍ ከተካረረ የሥልጣን ትግል በኋላ ዛሬ ለፓርላማ የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤያቸውን በማቅረብ ስንብት አድርገዋል።https://p.dw.com/p/GOhTስልጣናቸዉን የለቀቁት የሶማልያዉ ፕሪዝደንት አብዱላሂ ዩሱፍምስል APማስታወቂያ ዕርምጃው ሥርዓተ-ዓልባ እንደሆነች በቀጠለችው አገር የበለጠ የፖለቲካ ስጋትን የሚያስከትል ነው። ዩሱፍ ለመንግሥታቸው ድክመት የዓለምአቀፉን ሕብረተሰብ ድጋፍ መጓደል ምክንያት በማድረግ ወቀሣ ሰንዝረዋል። ሶማሊያ ከእንግዲህ ወዴት? አዜብ ታደሰ የፖለቲካ ምሑር የሆኑትን ረዳት ፕሮፌሰር መድሃኔ ታደሰን አነጋግራለች።