ውዝግቦችኢትዮጵያ
አማራ ክልል ጦርነቱ የላሊበላ አስጎብኚዎች ላይ ጫና አሳድሯል
ማክሰኞ፣ ኅዳር 24 2017ማስታወቂያ
በአማራ ክልል በመንግስትና በፋኖ ታጣቂ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ በሚገኘዉ ጦርነት ምክንያት በላሊበላ ከተማና ዙሪያዉ የቱሪስት አስጎብኚዎች ለኑሮ ችግር መዳረጋቸውን ገለጡ ። በአካባቢው የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ሀገር ጎብኚዎችን እያስተናገዱ ባለመሆኑ አስጎብኞች ለከፋ የኢኮኖሚ ችግር መዳረጋቸዉን ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል ።
የዓለም ቅርስ የሆኑት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያን በርካቶች ይጎበኙ ነበር
በላሊበላ ከተማና አካባቢዉ ያሉ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን በርካታ የዉጭ ሀገርና የሀገር ዉስጥ ጎቡኞ በየአመቱ የሚጎበኙት ሲሆን ማኅበረሰቡም ቱሪዝምን ብቸኛ የገቢ ምንጭ በማድረግ መተዳደሪያዉ አድርጎ ቆይቷል ።
ባለፉት አራት ዓመታት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ባለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ በአካቢዉ በመንግስትና በፋኖ ታጣቂ ኃይሎች መካከል ባለ ግጭት ቱሪስቶች ወደ ስፍራዉ ባለመምጣታቸዉ 200 የሚደርሱ የላሊበላና አካባቢዉ አስጎብኞች ለተለያየ ችግር መዳረጋቸ አቶ እስታሉ ቀለሙ የላሊበላ ከተማ አስጎብኝ ማኅበር ፕሬዝደንት ይናገራሉ ።
45 ሆቴሎች ሙሉ በሙሉ ሥራ ማቆማቸዉ ይነገራል
የላሊበላ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዲያቆን አዲሴ ሲሳይ በከተማዋ 45 የሚደርሱ ሆቴሎች ሙሉ በሙሉ ሥራ ማቆማቸዉን የገለፁ ሲሆን የቱሪዝም እንቅስቃሴዉን ለማነቃቃትም በመጭዉ የገና በአል ላይ ቱሪስቶች ወደ አካባቢዉ እንዲመጡ እየተሠራ ነዉ ብለዋል ።
ኢሳያስ ገላው
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ