1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሁለት ጉምቱ ፖለቲከኞች ስደት አንድምታ

ዓርብ፣ ነሐሴ 26 2015

ከሰሞኑ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ እና ታዋቂው ፖለቲከኛ አንዳርጋቸው ጽጌ በኢትዮጵያ የሰላማዊ ፖለቲካ ምህዳር ጠቧል በማለት ከኃላፊነት እስከ ሀገር መልቀቅ የደረሰ ውሳኔ ላይ መድረሳቸው በስፋት ተዘግቧል። አንድምታው ምን ይሆን ?

https://p.dw.com/p/4VrFa
Äthiopien Politiker Bekele Gerba
ምስል Addis Standard Magazine

አንጋፋ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሩ እና ጉምቱ ፖለቲከኛው ከሀገር መውጣት እና የፖለቲካው ምህዳር

የሁለት ጉምቱ ፖለቲከኞች ስደት አንድምታ

ከሰሞኑ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ እና ታዋቂው ፖለቲከኛ አንዳርጋቸው ጽጌ በኢትዮጵያ የሰላማዊ ፖለቲካ ምህዳር ጠቧል በማለት ከኃላፊነት እስከ ሀገር መልቀቅ የደረሰ ውሳኔ ላይ መድረሳቸው በስፋት ተዘግቧል። ለመሆኑ የፖለቲከኞቹ ከሀገር መውጣት ብሎም በሌላ ሀገር ጥገኝነት እስከመጠየቅ ያደረሳቸው  አንድምታ ምን ይሆን? በአገሪቱ የፖለቲካ ሂደት ላይስ  የሚያሳድረው ተጽእኖ ምን ይሆን?

ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስታዊ ለውጥ በመጣበት 2010 ዓ.ም. በተለያዩ መንገዶች የተፈረጁ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ አገር ውስጥ ተመልሰው ሰላማዊ ትግል እንዲያደርጉ ተጠይቀው ሁሉም በሚባል ደረጃ ወደ አገር ቤት መመለሳቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ይሁንና ያ ሁሉንም በሰላማዊ መንገድ ያሳትፋል የተባለው የፖለቲካ ምህዳር የመጥበብ ጥያቄ ይቀርብበት የጀመረ ደግሞ እምብዛም ዓመታት ሳይጓዝ ነበር፡፡ እንደውም በቅርቡ እራሳቸውን ከፓርቲ ፖለቲካ አመራርነት ማግለላቸውን ያስታወቁት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ እና የቀድሞ የግንቦት ሰባት አመራር የነበሩ ፖለቲከኛ አንዳርጋቸው ጽጌ በአገሪቱ ጠቧል ያሉት የፖለቲካ ምህዳር ለሰላማዊ የፖለቲካ ስራም የማይመች ነው በማለት ከሰሞኑ ትችት ሰንዝረው ወደ አገር ውስጥም እንደማይመለሱ በተናጥል አሳውቀዋል፡፡የአቶ በቀለ ገርባ ከፓርቲ ፖለቲካ መገለልና አሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸው 

ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስታዊ ለውጥ በመጣበት 2010 ዓ.ም. በተለያዩ መንገዶች የተፈረጁ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ አገር ውስጥ ተመልሰው ሰላማዊ ትግል እንዲያደርጉ ተጠይቀው ሁሉም በሚባል ደረጃ ወደ አገር ቤት መመለሳቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡
ከሰሞኑ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ በኢትዮጵያ ጠቧል ያሉት የሰላማዊ ፖለቲካ ምህዳር እራሳቸውን ከፓርቲ ፖለቲካ ከኃላፊነት ለማንሳት ውሳኔ እንዳበቃቸው አንስተዋል፡፡ምስል DW/M. Haileselassie

የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር ራሔል ባፌ ይህ ለአገሪቱ ፖለቲካ ጥሩ ምልክት አይደለም ሲሉ አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬለ ሰጥተዋል፡፡ “በርግጥ ፖለቲካ ምህዳሩ ጠቧል፡፡ ግን በጋራ በመሆን ከሩቅ ሳይሆን በቅርበት እዚሁ በመታገል መፍታት ይበጃል የሚል እምነት ነው ያለኝ” ሲሉም አስተያየታቸውን አክለዋል፡፡

በሰላማዊ መንገድ ያሳትፋል የተባለው የፖለቲካ ምህዳር የመጥበብ ጥያቄ ይቀርብበት የጀመረ ደግሞ እምብዛም ዓመታት ሳይጓዝ ነበር፡፡
የቀድሞ የግንቦት ሰባት አመራር የነበሩ ፖለቲከኛ አንዳርጋቸው ጽጌ በአገሪቱ ጠቧል ያሉት የፖለቲካ ምህዳር ለሰላማዊ የፖለቲካ ስራም የማይመች ነው በማለት ከሰሞኑ ትችት ሰንዝረው ወደ አገር ውስጥም እንደማይመለሱ በተናጥል አሳውቀዋል፡፡ ምስል Andargachew Tsige

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ፖለቲከኛ ጥሩነህ ገምታ በፊናቸው በሰጡን አስተያየት የኢትዮጵያ መሰረታዊ ችግር ፖለቲካዊ ነው ይላሉ፡፡ “የፖለቲካ ችግሩ መገለጫውም አንዱ አሳታፊነት የለውም፡፡በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ ሙሉ ለሙሉ መዘጋቱን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ገለጹ ስልጣን ከያዘው አካል ጋር ትስስር ያላቸው ብቻ ሲጠቀሙ ነው የሚስተዋለው፡፡ ይህ ለዘመናት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ነው” ብሏል፡፡ የፖለቲካ ምህዳሩ እጅጉን ጠቧል ያሉት ፖለቲከኛ ጥሩነህ በተለይም የፓርቲያቸው ኦፌኮ ጽህፈት ቤቶች ከመዘጋት እስካ አመራሮችና አባላቱ መሳደድ የዚህ መገለጫ ነው ሲሉም ወቀሳቸውን ሰንዝረዋል፡፡ ሰሞኑን ከፓርቲ ኃላፊነታቸው መገለላቸውን ያሳወቁት ጓዳቸው ፖለቲከኛ በቀለ ገርባም የዚሁ ሰለባ ነው በማለት ገልጸውአቸዋል፡፡ የዜጎች ንቃተህሊና በማሳደግ የፖለቲካ ተሳትፏአቸውን በማሳደግ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት ያለበት ፍጹም ዴሞክራሲያዊና ከሙስና የጸዳ መንግስትን በሰላማዊ ትግል መገንባት ፓርቲያቸው ግብ አድርጎ እንደሚሰራም በሰጡን ማብራሪያ አስቴዬታቸውን አጋርተዋል፡፡

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ፖለቲከኛ ጥሩነህ ገምታ በፊናቸው በሰጡን አስተያየት የኢትዮጵያ መሰረታዊ ችግር ፖለቲካዊ ነው
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ፖለቲከኛ ጥሩነህ ገምታ“የፖለቲካ ችግሩ መገለጫውም አንዱ አሳታፊነት የለውም፡፡ ስልጣን ከያዘው አካል ጋር ትስስር ያላቸው ብቻ ሲጠቀሙ ነው የሚስተዋለው ብለዋል። ምስል Seyoum Getu/DW

ፖለቲከኛ ራሔል ባፌም የመፍትሄ ሃሳብ ያሉትን ሲያመላክቱ፤ የፖለቲካ ምህዳር መጥበብ ጥያቄ አለኝ ያለውን የትኛውንም ኃይል እልባት ወደ ማያመጣው የትጥቅ ትግል በመምራት ችገግሮችን የሚወሳስብ እንደመሆኑ መንግስትም ሆነ ተፋላሚ ኃይላት ሁሌም ለድርድርና ውይይት ስፍራ ሊሰጡ ይገባል ነው ያሉት፡፡