የትራምፕ ትዕዛዝ እና የሶማሌ ማህበረሰብ
ረቡዕ፣ ጥር 24 2009ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ካፀደቁት በኋላ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ተግባራዊ መሆን የጀመረው የጉዞ እገዳ ሰለባ ከሆኑት መካከል በአሜሪካን የሶማሌ ማህበረሰብ አባላት ይገኙበታል ። ትራምፕ እገዳውን ከመፈረማቸው ከሁለት ቀናት በፊት 90 ሶማሌዎች ከአሜሪካን እንዲባረሩ ተደርጓል ። ትዕዛዙ ከተላለፈ በኋላ ደግሞ የአሜሪካን ቋሚ የሥራ እና የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ሶማሊያውያን ለጉዞ በተለያዩ አውሮፕላን ጣቢያዎች በተገኙበት ወቅት መታሰራቸው እና መንገላታታቸውን ሶማሊያውያን ይናገራሉ ። ከትራምፕ ትዕዛዝ በኋላ በመወሰድ ላይ ባሉት በነዚህ እርምጃዎች አሜሪካ የሚኖሩ የሶማሌ ማህበረሰብ አባላት በፍርሃት መዋጣቸዉን የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዘግቧል ።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ