1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአቶ በቀለ ገርባና የአቶ ጀዋር መሐመድ የፍርድ ቤት ዉሎ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 30 2012

አቶ በቀለ ገርባን እና አቶ ጀዋር መሐመድ የክስ መዝገቦች ላይ በተጠርጣሪነት የቀረቡ 14 ሰዎች ላይ ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ ምስክሮችን እንዲያሰማ ብይን ሰጥቷል። የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በዛሬው ውሎው በስነስረዓት ህጉ መሰረት ዓቃቤ ህግ ያቀረበው ምስክሮች በዝግ ችሎት ይሰሙልኝ » የሚለውን ጥያቄ ተቀብሎታል።

https://p.dw.com/p/3gYa7
Symbolbild Justiz Richter Gericht Richterhammer
ምስል picture-alliance/dpa/U. Deck

የአቶ ጀዋር መሐመድ እና የአቶ በቀለ ገርባ የፍርድ ቤት ውሎ

አቶ በቀለ ገርባን እና አቶ ጀዋር መሐመድን ጨምሮ በእነርሱ የክስ መዝገቦች ላይ በተጠርጣሪነት የቀረቡ 14 ሰዎች ላይ ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን እንዲያሰማ ብይን ሰጥቷል። የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በዛሬው ውሎው በስነስረዓት ህጉ መሰረት ዓቃቤ ህግ ያቀረበው ምስክሮች በዝግ ችሎት ይሰሙልኝ » የሚለውን ጥያቄ ተቀብሎታል። በዚህም የምስክሮችን የቅድመ ምርመራ ምስክርነት ቃል ለመቀበል ለፊታችን ነሐሴ 04/2012 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

 ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሐመድ