1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ቆላማ አካባቢዎችን ክፉኛ የጎዳው ድርቅ

እሑድ፣ ጥር 29 2014

አርብቶ አደሮች በሚያመዝኑባቸው በቆላማ አካባቢዎች እንሰሳትን የጨረሰው ድርቅ በህጻናትና ሴቶች ላይም ጉዳት እያደረሰ ነው። ኦቻ በነዚህ አካባቢዎች ከ6.4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አስታውቋል። በነዚህ አካባቢዎች በመጪዎቹ ወራት ዝናብ ካልጣለ ድርቁ  ከአሁኑም ተባብሶ የሰው ሕይወት እንዳያጠፋ ተፈርቷል።

https://p.dw.com/p/46YYf
Südostäthiopien | Dürre in Borena
ምስል Seyoum Getu/DW

ቆላማ አካባቢዎችን ክፉኛ የጎዳው ድርቅ

ተፈጥሮ ፊቷን ባዞረችባቸው የደቡብና ደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ቆላማ አካባቢዎች፣ድርቅ በቅርብ ጊዜ ታሪካቸው አይተው የማያውቁት የተባለ ጉዳት አድርሷል። በሶማሌ ክልል በምስራቅና ደቡብ ኦሮምያ በመደበኛ ዝናብ እጥረት ምክንያት መኖና ውኃ በመጥፋቱ እንሰሳት እንደ ቅጠል ረግፈዋል። በኦሮምያ ቦረና ዞን ብቻ ድርቁ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ እንሰሳትን ሕይወት አጥፍቷል። በሶማሌ ክልልም እንዲሁ ግመሎችን ጨምሮ በርካታ እንሰሳት ሞተዋል። አርብቶ አደሮች በሚያመዝኑባቸው በነዚህ አካባቢዎች እንሰሳትን የጨረሰው ድርቅ በህጻናትና ሴቶች ላይም ጉዳት እያደረሰ ነው። የተመ የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባባሪዎች ቢሮ በምህጻሩ ኦቻ ከአንድ ወር በፊት ባወጣው ዘገባ በድርቅ በተጎዱት በነዚህ አካባቢዎች ቁጥራቸው ከ6.4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አስታውቋል።ከመካከላቸው 3 ሚሊዮን ያህል በሶማሌ ክልል ፣2.4 ሚሊዮኑ በምሥራቅ ኦሮምያ እንዲሁም አንድ ሚሊዮኑ በደቡብ ኦሮምያ እንደሚገኙ ገልጿል። በነዚህ አካባቢዎች በመጪዎቹ ወራት ዝናብ ካልጣለ ድርቁ  ከአሁኑም ተባብሶ የሰዎች ሕይወት እንዳይጠፋ ማስጋቱ አልቀረም። በቆላማ አካባቢዎች ድርቅ ያስከተለው ጉዳት፣ ወደፊት የሚያሰጋው አስከፊ ችግርና መፍትሄው የዛሬው እንወያይ መነጋገሪያ  ነው።በዚህ ላይ የሚወያዩ እንግዶቻችን ክተር ቃሲም ጉዮ በኦሮምያ ክልል የቦሮና ዞን ግብርና ቢሮ ምክትል ሃላፊና የእንሰሳት ሀብት ልማት ሃላፊ፣አቶ ደበበ ዘውዴ የፌደራል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ህዝብ ግንኙነት አቶ ዛይድ ኢብራሂም አሊ የሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ተጠሪ ናቸው።ሙሉውን ውይይት ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን ማዕቀፍ ይጫኑ፦

Äthiopien | Dürre in Borena
ምስል Firaol Wako/PHD

ኂሩት መለሰ