የተመድ አስተያየት
ሐሙስ፣ ጥቅምት 24 2009ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ወታደሮቿን ከሶማሊያ ስታስወጣ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዳላሳወቀች ተነገረ ። በተመድ የፖለቲካ ጉዳዮች ተጠሪ ሆዜ ሉስየስ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ድርጅታቸው ኢትዮጵያ ከሶማልያ ወታደሮችዋን እንደምታስወጣ አስቀድሞ አልተነገረውም ። የቀድሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያ በራስዋ ወጭ ሶማሊያ ያዘመተቻቸውን ወታደሮቿን በገንዘብ ችግር ምክንያት እንዳስወጣች ባለፈው ሳምንት ተናግረው ነበር ። የመንግሥታቱ ድርጅት ባለሥልጣን ሉስየስ እንዳሉት ድርጅታቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች በመውጣታቸው የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት ሌሎች አባላትን እየጠየቀ መሆኑን አስታውቀዋል ።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ