1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ጎረቤቶችን ያፋጠጠው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ምርጫ

Eshete Bekele/MMTሰኞ፣ ሚያዝያ 7 2016

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማኅማት ከ2009 ጀምሮ ከያዙት ሥልጣን በሚቀጥለው ዓመት ይለቃሉ። የኮሚሽኑ ቀጣይ ሊቀ-መንበር አስራ አራት ሀገራት ከሚገኙበት የምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና የሚመረጥ ይሆናል። እስካሁን ከሦስት የኢትዮጵያ ጎረቤቶች ዕጩዎች ለአፍሪካ ኮሚሽን ሊቀ-መንበርነት እንደሚወዳደሩ አስታውቀዋል። የኬንያው ራይላ ኦዲንጋ፣ የሶማሊያዋ ፋውዚያ ይሱፍ አዳም እና የጅቡቲው ማሕሙድ አሊ ይሱፍ ለሊቀ-መንበርነቱ የመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው አሳውቀዋል። ሦስቱም ዕጩዎች የየመንግሥታቶቻቸው ድጋፍ አላቸው። ሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ ክፍለ አኅጉር ሀገራት ዕጩዎች ካሏቸው እስከ ግንቦት ወር ማቅረብ ይችላሉ።

https://p.dw.com/p/4eoOe
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ስለዚሕ ዝግጅት

ስለዚሕ ዝግጅት

DW I Podcast Cover - Feature der Woche, Amharisch Mohammed Negash
ምስል DW

ማሕደረ ዜና

ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀርብበታል። አዘጋጅ፣ ነጋሽ መሐመድ