1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

የዐድዋ ድል በዓል በአሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተከበረ

ሰኞ፣ የካቲት 28 2014

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትናንት ባካሄደው የዐድዋ ድል አከባበር ላይ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋና በተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ተገኝተዋል። በተመሳሳይ፣በአትላንታ ጆርጂያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የዐድዋ ድል፣ የሰማዕታት ቀን መታሠቢያና የካራማራ ድል በዓልን አክብረዋል።

https://p.dw.com/p/487sd
Äthiopien | Adwa Feierlichkeiten
ምስል Tariku Hailu/DW

የዐድዋ ድል 126ኛው ዓመት በአሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በድምቀት ተከበረ።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትናንት ባካሄደው የዐድዋ ድል አከባበር ላይ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋና በተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ተገኝተዋል። በተመሳሳይ፣በአትላንታ ጆርጂያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የዐድዋ ድል፣ የሰማዕታት ቀን መታሠቢያና የካራማራ ድል በዓልን አክብረዋል። በአትላንታ የኢትዮጵያ ማኀበረሰብ ማኀበር የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው ስነስርዓት ላይ የተገኙት ታዋቂው የታሪክ ምሑር ኘሮፌሰር ኀይሌ ላሬቦ የዐድዋ ድል የጥቁሮችን የትግል እንቅስቃሴ ያስጀመረበትን ታሪካዊ ዳራ ለበዓሉ ተሳታፊዎች አስረድተዋል።

ታሪኩ ኃይሉ 

ታምራት ዲንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ