1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ህጻናትና እናቶችን ለከፋ ችግር የዳረገው የሰሜን ወሎ ቡግና ወረዳው የምግብ እጥረት

ሰለሞን ሙጬ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 11 2017

አቶ ገብረመስቀል አለሙ 7ሺህ የሚሆኑእድሜያቸዉ ከ5 አመት በታች የሆነ ህፃናት በስርዓተ ምግብ ችግር መጎዳታቸውንና ከ3ሺህ በላይ ነፍሰጡር እናቶችም ተመሳሳይ ችግር እንደደረሰባቸው ፣ከምግብ እጥረቱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ምንም አይነት ሞት በጤና ተቋማት አለመመዝገቡን ገልጸው ከድርቁ ጋር ተያይዞ ግን ተጓዳኝ ህመሞች ተከስተዋል ብለዋል።

https://p.dw.com/p/4oQcj
Somalia | Mutter mit Kind im Krankenhaus
ምስል Guy Peterson/AFP/Getty Images

«በምግብ እጥረት ከ10 ሺህ የሚበልቹ ህፃናትና እናቶች ለከፋ ችግር ተዳርገዋል።»

 


በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በተከሰተ ድርቅና የምግብ እጥረት ቁጥራቸዉ ከ10 ሺህ የሚልቅ ህፃናትና እናቶች ለከፋ ችግር መዳረጋቸዉ ተገለፀ። በአካባቢዉ ባለፈዉ አንድ አመት በመንግስትና በፋኖ ታጣቂ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ በሚገኘዉ ጦርነት አልሚ ምግብና መድኃኒት ካለመግባቱ ጋር በተያያዘ በቡግና ወረዳ በሚገኙ 16 ቀበሌዎች ችግሩ ሊከሰት ችሏል ሲሉ የብግና ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጌታየ ካሳዉ ገልፀዋል።

በአማራ ክልል ከ100 ሺህ በላይ ህፃናት ለከፋ የምግብ እጥረት ተዳርገዋል
በወረዳዉ ዋረቡ 03 ቀበሌ ኗሪ የሆኑት ወይዘሮ በላይነሽ አስረስ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በአካባቢዉ በተፈጠረ ድርቅና የምግብ እጥረት ምክንያት ጡታቸዉ ደርቆ ለስምንት ወር ልጃቸዉን ጡት ማጥባት አለመቻላቸዉን ይናገራሉ። በተከሰተዉ ድርቅና የምግብ እጥረት ምክንያት ወደ ህክምና ተቋማት የሚመጡ ህፃናት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል የሚሉት የወረዳዉ ኗሪ መላከ ብርሀን ዮሴፍ ታረቀኝ ህፃናቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ እንዳሉ ይገልፃሉ። በባለፈዉ አንድ ዓመት ዉስጥም አልሚ ምግብና መድኃኒት ወደ ወረዳዉ ካለመግባቱ ጋር በተያያዘ ሁለት ህፃናት መሞታቸዉን የገለፁት አቶ ዉዱ ፀጋዉ አሁንም ህፃናቱ በአስከፊ ደረጃ ላይ እንዳሉ ይናገራሉ ። የወረዳዉ ጤና ጽፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረመስቀል አለሙ እንደገለፁት አካባቢዉ በሰዉ ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች የተጎዳ በመሆኑ እናቶችና ህፃናት ከፍተኛ ለሆነ የምግብ እጥረት ችግር ተዳርገዋል ይላሉ።

በምግብ እጥረት የተጎዳ ህጻን
በምግብ እጥረት የተጎዳ ህጻን ምስል Sun Ruibo/Unicef/Photoshot/picture alliance

ለረሃብ የተጋለጡ ህጻናት በትግራይ

7000 የሚሆኑ እድሜያቸዉ ከ5 አመት በታች የሆኑ ህፃናት በስርዓተ ምግብ ችግር የተጎዱ ሲሆን እንዲሁም ከ3000 በላይ የሆኑ ነፍሰጡር እናቶችም ተመሳሳይ ችግር ደርሶባቸዋል በማለት ይናገራሉ። እስካሁን ከምግብ እጥረቱ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ሞት በጤና ተቋማት አለመመዝገቡን የገለፁት አቶ ገብረመስቀል  አለሙ  ከድርቁ ጋር ተያይዞ ግን ተጓዳኝ ህመሞች ተከስተዋል ብለዋል። የሰሜን ወሎ ዞን የስነ-ምግብ ባለሙያ አቶ ጌትነት ብርሀኑ በበኩላቸዉ በወረዳዉ ያሉ 4 ጤና ጣቢያዎች ህፃናትና እናቶች በማከም ላይ መሆናቸዉን ገልፀዉ ችግሩ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠዉ ይገባል ብለዋል።አሁን በአካባቢዉ በመንግስትና በፋኖ ታጣቂ ኃይሎች መካከል የሚካሄደዉ ጦርነት ከቀጠለና ሰብዓዊ ድጋፋ በአካባቢዉ መድረስ ካልቻለ ከዚህ የባሰ ችግር ሊከሰት እንደሚችልም ተናግረዋል።

«ሰዎች በርሐብ እየሞቱ ነው»የተፈናቃዮች አቤቱታ
ከሰሞኑ ዪኒሴፍ እና የአለም ምግብ ድርጂት በአካባቢዉ ድጋፍ ማድረግ መጀመራቸዉም ሊበረታታ የሚገባዉ ተግባርም ነዉ ብለዋል።
የቡግና ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጌታየ ካሳዉ ባለፈዉ አንድ አመት አካባቢዉ በፋኖ ኃይሎች ቁጥጥር ስር በመሆኑ ተቋርጠዉ የነበሩ የአልሚ ምግብና መድኃኒት አቅርቦት በአሁን ጊዜ ከሀይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎችና የጤና ባለሙያዎች ጋር በመነጋገር ድጋፉ ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲዉል  ወደ አካባቢዉ እንዲገባ ተደርጓል ብለዋል ።
ኢሳያስ ገላው
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ