ለሶርያ ስደተኞች መርጃ ዳጎስ ያለ ገንዘብ የተሰበሰበበት የለጋሾች ስብሰባ
ቅዳሜ፣ ሰኔ 10 2015ከትላንት በስቲያ ሐሙስ እዚህ ብራስልስ በተካሄደደው 7ኛው የሶሪያ መርጃ አለማቀፍ ጉባኤ፤ ከለጋሾች የ5.6 ቢሊዮን እርዳታ ቃል የተገባ መሆኑ ተገልጿል። ከዚህ ውስጥ 4.6 ቢሊዮን ዩሮ ለዚህ አመት ሲሆን 1 ቢሊዮኑ ለሚቀጥለው ለ2024 የሚተላለፍ ነው ተብሏል።
እርዳታው በሶሪያ ላሉና ሶሪያውያን ስደተኞች ለተጠለሉባቸው የጎረቤት አገሮች መርጃ የሚሆን ነው። ጆርዳን፣ ሊባኖስ፣ ቱርክ ኢራቅና ግብጽ በጦርነቱ የተፈናቀሉና የተሰደዱ ሶሪያውያን ስደተኞች በብዛት የሚገኙባቸውና ተጨማሪ እርዳታም የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፤ በያመቱ የሚደረገው የሶሪያ መርጃ አለማቀፍ የለጋሾች ጉባኤም፤ በሶሪያ ላሉት ብቻ ሳሆን በነዚህ አገሮች ለሚገኙ ሶሪያውያን መርጃ ገንዘብ የሚያሰባስብ ነው።
ከትላንት በስቲያ ሊዋጣ ቃል ከተገባው 5.6 ቢሊዮን ዩሮ ውስጥ ከአውሮፓ ኮሚሽን 2.1 ከአባል አገሮች ደግሞ 1.7 ቢዮን የሚሰበስብ ሲሆን፤ ከአውሮፓ ህብረት ባጠቃልይ 3.8 ቢሊዮን ዩሮ የተገኘ ወይም የተለገሰ ነው ተብሏል። በተጨማሪም አለማቀፍ ድጅቶች እና ለጋሾች የ4 ቢሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ቃል የገቡ ሲሆን፤ በድምሩም የ9.6 ቢሊዮን ዩሮ ብድር እና እርዳታ እንደተገኘ ታውቋል።
የሶሪያ ቀውስ በጎርጎሮሳዊው 2011 ከተጀመረ ወዲህ፤ የአውሮፓ ህብረት ሶሪያውያንን፤ በሶሪያና በጎረበት አገሮች ለመርዳት 30 ቢዮን ዩሮ ያሰባሰብና የለገሰ መሆኑም ተገልጹል። በትናንቱ አመታዊ የለጋሾች ስብሰባ፤ የ57 አገሮችና የ30 አለማቀፍ ድርጅቶች ተወካዮችና ለኡካን ተግንተዋል። የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴርሽ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልክት፤ በስብሰባው የተገኙትን አመስግነው፤ በአስከፊው ጦርነት ምክኒያት ከአስር አመት በላይ ሶሪያውያን ለሞት ስደትና እንግልት መዳረጋቸው የሚያሳዝን መሆኑን ገልጸዋል። እያደገ የመጣውን የስደተኞች ፍላጎት ለማሟላትና ሶሪያውያንን ያስጠጉ አገሮችን ለማገዝ ለጋሾች እርዳታቸውን እንዲያሳድጉም ተመጽነዋል።
“እያደገ የመጣውን የስደተኞች ፍላጎት ለማሟላትና የሶሪያ ስደተኞችን ባስጠለሉ አገሮች ላይ የወደቀውን የገንዘብ ጫና በመገንዘብ ለጋሾች የምትችሉትን ሁሉ እንድታደርጉ ጥሪ አቀርባለሁ በማለት የሶሪያ ጦርነት የሶሪያውያን ብቻ እንዳልሆነና የተፈጠረውን ሁለንተናዊ ቀውስ የማቃለሉ ሀለፊነትም የጋራ መሆኑን አስገንዝበዋል። በሶሪያ በአሁኑ ወቅት 30 ሚሊዮን ሶሪያውያን የሚኖሩት በዕርድታ መሆኑንና 10.5 ሚሊዮን ስደተኖችም በጎረቤት አገሮች ያሉ ተረጂዎች መሆናቸውንም ዋና ጸህፊው ጠቅሰዋል።
የብራስልሱን አመታዊ የለጋሾች ስብሰብ፤ ካስተባበሩትና ከመሩት አንዱ የሆኑት የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ሚስተር ጆሴፕ ቦሪየል በሰጡት መግለጫም፤ የሶሪያ ችግር 12 አመት የዘለቀ መሆን ጠቅሰው ምንም እንኳ በአሁኑ ወቅት ከሩሲያ የዩክሪየን ወረራ በተጨማሪ ለሎች ችግሮች በደቡብና ምስራቅ ያሉ በሆንም፤ ዛሬም ሶሪያን ለመርዳት የተገናኙ መሆኑን ገልጸዋል። “ ዛሬ ለሰባተኝ ግዜ በሶሪያ ችግሮች ላይ ለመወይየትና እርታት ለማሰባሰብ ተገናኝተናል። የአውሮፓ ህብረት ለሶሪያ ትልቁ ለጋሽ አካል ነው” በማለት የሶሪያ ሁኔታ የህብረቱ ዋና አጀንዳ ሆኖ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።
ስብሰብው የእርዳታ ማስባሰቢያ ፕሮግራም ብቻ ሳይሆን በሶሪያ የፖለቲካ ሁኒታ ላይና ፤ችግሩ ለዘለቄታ ፖለቲካቂ መፍትሄ ስለሚያገ\ኝበትም ውይይት የሚደረግበት እንደሆነም በመጥቀስ፤ የሶሪያን ችግር ለመፍታት የተባበሩ መንግስታት ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን በስብሰብው የተጠየቀ መሆኑንም አንስተዋል ።
ከዚህ አንጻር የህብረቱን አቋም ሲገልጹም፤ “ የአውሮፓ ህብረት በሶሪያ ላይ የሚክተለው ፖሊስ አልተለወጠም። ትክክለኛና አጠላይ የሽግግር ስራት ሳይመሰረት ከአሳድ መንግስት ጋር አብረን አንሰራም፤ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትም አንፈጥርም” ብለዋል። ይህ እስከሚሆን በሶሪይ መንግስት ላይ የተጣለው ማዕቀብ የሚቆይ መሆኑን የገለጹት ሚስተር ቦርየል፤ ለጤናና ለሎች ሰባዊ እርድታ የሚሰጠው እርዳታ ግን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። በርካታ አገራት በአሁኑ ወቅት ከሶርያ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት እያደሱ ሲሆን፤ ከሳምንታት በፊትም የአረብ ሊግ ሶሪያን ወደ ሊጉ ዳግም እንድትቀላቀል የፈቀደ መሆኑ ታውቋል።
ገበያው ንጉሴ
እሸቴ በቀለ