1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርትአፍሪቃ

«መንታ መንገድ» ድራማ ክፍል 2

Chrispin Mwakideu/Mantegaftot Sileshiረቡዕ፣ ነሐሴ 27 2007

ወጣቶቹ ገፀባህሪያት፥ ምሕረት፣ ዳንኤል፣ ንጉሤና ሌሎቹም ባለታሪኮች ድርጊቶቻቸውና አንዳንድ አዳዲስ፣ አሳሳች ሁኔታዎች ያመጧቸውን ሁሉ መጋፈጥ ይኖርባቸዋል።

https://p.dw.com/p/1E2bK
Crossroads_Staffel 2_1024x576.jpg
ምስል DW

የዳንኤል ቤተሰቦች በሚኖሩበት ላቦሪያ የርስ በርስ ጦርነት ተቀስቅሷል፤ ቤተሰቦቹም ችግር ላይ ሳይወድቁ አልቀሩም። ዳንኤል ሌላ ስፍራ ከቤተሰቦቹ ርቆ ቦንጎ አካዳሚ ውስጥ በመገኘቱ ግን ለጊዜው ከአደጋ ውጪ ነው። ይሁንና ያ ማለት ችግሮችን አስወግዷል ማለት አይደለም። የሴቶች አቀራረቡ ችግር ውስጥ ይጥለዋል። እናስ ኃላፊነቱን ለመረከብ ዝግጁ ነው?

ምሕረት እራሷ በጭንቅላቷ በርካታ ነገር ነው የሚመላለሰው። መንታ ወንድሞቿ ቅዱስ እና ብሩክ በስተመጨረሻላይ ወደ ቤተሰባቸው ይመለሳሉ፤ ግን ምን አጋጥሟቸውይሆን? ለምንስ ይሆን መጥፎ ህልሞችን በተደጋጋሚ የሚያልሙት፤ ለምንድን ነው ብሩክስ እንዲያ ሳሉ የጠናበት?ዳግም የሚገናኘውን ቤተሰብ ሌላም ችግር ይገጥመዋል።የምህረት አባት አቶ ሙላቱ ከፖሊስ እና በስተመጨረሻ ላይ እምቢኝ ብላ ከምትነሳባቸው ባለቤታቸው ዘንድችግር ይገጥማቸዋል። ይሁንና ይህ ሁሉ ከምህረት ታላቅምሥጢር ጋር የሚወዳደር አይደለም…

ትምህርት ቤት ውስጥ ምህረት ከትዕግስት ጋር ያላት ጓደኝነት ይፈተናል፤ ንጉሤም በክፍሉ ምርጥ ተማሪነቱ አይዘልቅም…

የ«መንታ መንገድ» ወጣት ትውልዶች በሁለተኛው ዙርድራማ በርካታ ነገሮችን መጋፈጥ ይኖርባቸዋል። ይሁንና እያንዳንዱን ነገር ለብቻቸው መጋፈጥ እንደሌላባቸውምይረዳሉ እናም ነገሮች ጠንከር ሲሉባቸው እርስ በርስ ይተባበራሉ።