ሥጋት የጋረደዉ የኢትዮጵያ-ሶማሌ አርብቶ አደሮች የአኗኗር ዘይቤ
ሥጋት የጋረደዉ የኢትዮጵያ-ሶማሌ አርብቶ አደሮች የአኗኗር ዘይቤ
ሊገመት የማይችል የወደፊት ጊዜ
በሰሜናዊዉ ሶማሌ የኢትዮጲያ ግዛት፤ ጋድ መንደር ዉስጥ የምትኖር የአራት ዓመቷዋ ሳፋ በእናቷዋ ነጠላ ስር ተሸፍናለች። «አርብቶ አደርነት ጥሩ ሕይወት ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም በቂ ምግብ፣ ወተት እና ንጹሕ አየርን በማስገኘቱ ነዉ» ትላለች የ32 ዓመቷ የጋድ እናት ሙሚና ቡህ። «ግን አሁን ያ ሁሉ ነገር የለም» የአርብቶ አደር ሕይወት ከባድ እየሆነ ስለመጣ ቤተሰቦቿዋ፣ እንደ ሌሎቹ አርብቶ አደሮች ሁሉ፣ በአንድ ሰፈራ ጣብያ ዉስጥ መቀመጥን መርጠዋል።
ድንበር የማይገድበዉ ሕይወት
አርብቶ አደሮች ዉድ ከሆኑት የቀንድ ከብቶች የሚያገኙትን የሥጋ ዉጤቶችን ጨምሮ፣ ወተትን ሁሉ በመነገድ ይጠቀማሉ። አርብቶ አደሮቹ ፍየሎቻቸዉን፣ በጎቻቸዉን፣ ከብቶቻቸዉንና ግመሎቻቸዉን ይዘዉ በኢትዮጵያ፣ በሶማሊያ እና በጅቡቲ በበራሃማዉንና ገላጣዉን መሬት እያቋረጡ ዉድ የሆነዉ ዉኃ እንዲሁም ለከብቶቻቸዉ መኖ ፍለጋን ሲዘዋወሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሰመረዉ ድንበር ምንም ትርጉም አይሰጣቸዉም።
ደምሳሹ «ሙሊያ»
በአፍሪቃ ቀንድ በተከሰተዉ ድርቅ የኅብረተሰቡን ማንነት የተመሠረተበትና የአኗኗር ዘይቤዉን ቀይሮአል የቀንድ ከብቶችን ሁሉ አዉድሟል። በዚህ አካባቢ ከ600, 000 በላይ የሚገመቱ የቀንድ ከብቶች ሞተዋል። «እንዲህ ያለ ነገር በጭራሽ አጋጥሞኝ አየዉቅም» ይላል የ65 ዓመቱ አርብቶ አደር ኤልቴስ ሙሴ ባሃ ። «ይህንን ድርቅ ሙሊያ ብለን ሰይመነዋል ይላል ሙሴ። ይህ ማለት ደግሞ መሬት ላይ ያለን ሁሉ ነገር የሚደመስስ ነገር ማለት ነዉ»
የጠፋዉ የኑሮ ዘይቤ
«ወደ አደኩበት ሕይወት ያለ ቀንድ ከበት መመለስ አንችልም» ስትል የ37 ዓመቷ ዳሃቦ ትናገራለች። ዳሃቦ በድርቁ ምክንያት ከቤቴሴቦቿ ጋር በፊት ስትኖርበት ከነበረዉ ቤትዋ ርቃ በፌዴቶ መጠሊያ ጣብያ መኖር ጀምራለችች። ግሬቡህ፣ የ45 ዓመቱ ባሏ በበኩሉ፣ «እኔ ኃላፊነት የሚሸከም አባት መሆን ነበረብኝ ይላልል። ግን አሁን ቢሆን ምንም የለኝም ፤ ቀንድ ከብቶቼን አጥቻለዉ፤ መልሼ ልገዛቸዉ አልችልም፣ ስለዚህ ቤተሰቤን የምረዳበት ሌላ መንገድ መፈለግ አለብኝ ሲል ተናግሮአል።
ሌላ ምርጫ የለም ግን ሁሉም ነገር መቆጠብ
«ልጆቼን በሦስት ቀን አንዴ ገላቸዉን አጥብ ነበር፣» ትላለች የ8 ልጆች እናትና የ38 ዓመቷ ሃል ማሃድ በጋድ መንደር ከጉድጓድ ዉኃ ለመቅዳት ስትሄድ። በፊት ከነበራቸዉ 60 ፍየሎችና በጎች አሁን 10 ብቻ ነዉ የቀርዋቸዉ። «አሁን በቀን የምንበላዉ ሁለት ግዜ ብቻ ነዉ፣ እንጄራ እና ሻይ ጠዋት፣ ከዛም ቀጥሎ በትንሽ ዘይት ማሽላ ወይም ሩዝ ሰርተን እራታችን እንበላለን። ለምሳሌ ሽንኩርት እና ሌላ ነግር በላዩ ላይ መጨመር አንችልም።
ጠንካራ ሰዎች
«አስቸጋሪ ሁኔታ የሚቋቋሙ እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች አናገኝም» ሲሉ የኦክስፋም የደርቅ መቋቋሚያ ሥራ አስከያጅ ፕቴር ስትሩእጅፍ ይናገራሉ። «እነሱ ከፍተኛ የድርቅ መቋቋምያ ዜዴዎችና ለእንስሳቶቻቸዉ መኖ ለመፈለግ የተወሳሰበ የእንቅስቃሴ ስልት አላቸዉ ባይ ናቸዉ።» ግን አሁን ወደ ሶማሌላንድ ባህር ዳርቻ ስሄዱ ምንም ሊያገኙ አልቻሉም እናም ሲመለሱ ብዙ እንስሳቶች አልቀዋል፣ ሌሎችም እንደምንም ተመልሰዋል።» የኢትዮጲያ መንግስት የቀሩትን እንስሳቶችን ለማዳን መኖ በማከፋፈል ላይ ይገኛል።
ያላቸዉን ጸጋ መጠበቅ
«እንስሳቶቹን ከከፍተኛ ሙቀት ለመጠበቅ ሰዎች የሚጠለሉበት ነገር ሰርተዉላቸዋል፤ ሌሎች ደግሞ የሚያገኙትን የርዳት ምግብ ከእንስሶቻቸዉ ጋር ይካፈላሉ» ሲሉ የአዉሮጳ ኮሚሽን የሰብዓዊ ርዳታና ስብል ጥበቃ «ECHO» ቃላ አቀባይ አኖዉክ ዴላፎርትር፣ አርብቶ አደሮቹ ለእንስሳቶቻቸዉ ያላቸዉን ጽኑ ፍቅር እንዴትነት ሲገልፁ ተናግረዋል። «ECHO» ኢትዮጲያ ድርቁን እንድትቋቋም በሚያዝያ ወር ብቻ 122 ሚሊዮን ዩሮ ለግሶአል።
ድርቁን ድል ለማድረግ
«ድርቁ ያመጣውን አደጋ ለመቀነስ ለየት ባለ መንገድ ማሰብ አለብን፣ ጉዳት በደረሰበት አካባቢ በኤኮኖሚ መርዳት አንዱ ነዉ» ሲሉ የ «ሴቬ ዘ ችልድረን» ሥራ አስካያጅ ጆን ግራም ገልፅዋል። አሁንም የኢትዮጵያ መንግስትና የዓለምአቀፉ ማኀበረሰብ አርብቶ አደሮቹን አዲስ በመስኖ የለሙ ቦታዎች አካባቢ ለማስፈር አንድ መረሃ-ግብር ላይ እየሰሩ ነዉ።
ሌላ አማራጭን ማሰብ
«ከመንግስት የእንስሳት መኖ የማከፋፈል ፕሮግራም ከተረዳን እድል ይኖረናል» የ50 ዓመቱ ኦስማን ካይሬ በጋድ መንደር ከሚገኙ የአርብቶ አደሮች ቡድን ጋር ሆኖ ለእንስሳቱ ከመንግስት የሚከፋፈለዉን መኖ በመጠባበቅ ላይ ሳለ እንደተናገረዉ፤ « ሌላዉ አማራጭ የመንግስትን የመልሶ ማስፈር ፕሮግራም ተጠቅመን ለግብርናና እንስሳትን ለማርባት ወደሚያመች ሁኔታ መጠቃለል ነዉ። ይህንን ለመቀበልም ዝግጁ ነን።
በምርጫቸዉ ባይሆንም ተጠልለዋል
በፌዴቶ መንደር የሚገኘዉ የመጠለያ ካምፕ ቀን ቀትር ላይ ያለዉ ከፍተኛ የፀሃይ ሁሉም ነገር ያቃጥላል። አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ቢኖርም ቅሉ ኑሮ ግን ቀጥለዋል። ልጆች በአቧራ በአቧራ ሆነዉ መጠልያ ዉስጥ ይጫወታሉ። በሌላ በኩል ሌሎች ቀጥሎ ሊመጣ ከሚችለዉ ችግር ጋር ተጠምደዋል። « በየዓመቱ ሌላ ድርቅ ያለ ይመስላል» ሲሉ ግሬቡህ ይናገራል። «ሁኔታዉ እንብዛም የሚሻሻል አይመስልም።»