በምስራቅ አማራ እየጨመረ የመጣዉ የህፃናት ጥቃት
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 18 2017በህፃናት ላይ የሚፈፀም ፃታዊ ጥቃት እየጨመረ መምጣቱን በደሴ ሪፈራል ሆስፒታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት ገለፀ
ማዕከሉ በምስራቅ አማራ ፃታዊ ጥቃት ለደረሰባቸዉ ሰዎች አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በያዝነዉ አመት እድሜያቸዉ ከሦሶት አመት ጀምሮ ባሉ ህፃናት ላይ ፆታዊ ጥቃት መፈፀሙን የማዕከሉ አስተባባሪ ሲስተር መዲና ወርቅነህ ይናገራሉ።
ጥቃቱ በአብዛኛዉ የጫት ዕፅ ተጠቃሚዎች የሚበዙበት ከተሞች ላይ ሀይቅ፣ ኮምቦልቻ፣ ባቲ እንዲሁም ከሚሴ በዝቶ መታየቱን ነዉ
የማዕከሉ መረጃ የሚያሳየዉ።
በምስራቅ አማራ ህፃናት ላይ የሚደርሰዉ ፃታዊ ጥቃት ቢጨምርም ተጎጂዎች ወደ ህግ አካል እየመጡ አይደሉም የሚሉት ሳጂን ፋጡማ አሊ አሁን በአካባቢዉ ያለዉ ጦርነት ተጎጂዎችን ወደ ህክምና ማዕከላት እንዳይመጡ እንቅፋት ሁኗል ነዉ የሚሉት።
ፃታዊ ጥቃት የሚፈፅሙ ወንጀለኞች ላይየሚወሰድ ቅጣት ከዋስትና መብት ጋር ተያይዞ በተገቢዉ መንገድ ተፈፃሚ እየሆነ አይደለም የሚሉት አቃቤ ህግ ወይዘሮ አደፋሽ አባተ በርካታ ወንጀለኞች ከዋስትና ጋር በተያያዘ ጥፋት ሰርተዉ ይሰወራሉ ብለዋል።
የህግ አተረጓጎም ልዩነት መኖርና ህጉ በራሱ ያለበት የአፈፃፀም ክፍተት አጥፊዎች ተገቢዉን ቅጣት እንዳያገኙ ምክንያት ነዉ የሚሉት በወሎ ዮንቨርስቲ የህግ ትምህርት ቤት መምህርና ጠበቃ አቶ አለሙ ዳኘዉ አሁን እየተሻሻለ የሚገኘዉ የወንጀል ስነስርዓት ህግ ሲፀድቅ የተፈጠረዉን የህግ ክፍተት ይሞላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።
ኢሳያስ ገላው
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ሂሩት መለሰ