1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በምዕራብ ወለጋ ዞን 338 ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ

ሐሙስ፣ ሰኔ 23 2014

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በተፈጸመው ጥቃት 338 ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ። መንግሥት ሰኔ 11 ቀን 2014 በተፈጸመው ጥቃት ስለተገደሉ ሰዎች ቁጥር መረጃ ሲያቀርብ የመጀመሪያ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪ ቢልለኔ ስዩም ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለቻ ሰጥተዋል።

https://p.dw.com/p/4DU1o
Äthiopien | PK Billene Seyoum | Sprecherin des Premierministers
ምስል Yohannes Geberegziabher/DW

የፕሬስ ሴክሬታሪ ቢልለኔ ስዩም መግለጫ

ሰላም እና መረጋጋት የመንግሥት ዋነኛ እና ቅድሚያ የሚሰጠው አጀንዳ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ገለፁ። 
መንግሥት ኦነግ ሸኔ ያለው የሽብር ቡድን ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ውስጥ በፈፀመው ግድያ ማዘኑን ገልጾ የዚህ ዓላማ በኦሮሞ እና አማራ ብሔሮች መካከል ልዩነት ለመፍጠር እና በአማራ ክልል ውስጥ ቀጣ ለመቀስቀስ ሆን ተብሎ፣ ታቅዶበት የተሠራበት መሆኑ ተነግሯል።
የደረሰው ጉዳት በፌዴራል ፖሊስ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን የተናገሩት የጠቅላይ ሚኒስቴር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢለኔ ስዩም ኢትዮጵያውያን አንድነትን እንዲያጠናክሩ ማድረግ ይገባል የሚል መልእክት አስተላልፈዋል።

ወደ ትግራይ ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች የሰብዓዊ ድጋፍ እየደረሰ መሆኑንም በቁጥር አስደግፈው ዘርዝረዋል። ለመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ መዘጋት የነዳጅ እጥረት መሆኑ ተጠቅሶ ስለሚነገረው መረጃ ማስተባበያ የሰጡት ኃላፊዋ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም እና ከአለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የተገኙ ሦስት የተለያዩ አውሮፕላኖች ጥቅም ላይ እየዋሉ መሆኑንና ነዳጅ ከአዲስ አበባ እየሞሉ እያገለገሉ ምሆኑን አስታውቀዋል።
የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በሰላም አማራጭ እንዲታይ የመንግሥትን ውሳኔ ያስታወሱት ቢለኔ መንግሥት የአፍሪካ ሕብረት የሰላም ማፈላለግ ጥረት ደጋፊ እና ለሂደቱም ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረወል።
ከሰሞኑ የሱዳን መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ የሰነዘረው ውንጀላ ተቀባይነት የሌለውና የመከላከያ ሠራዊት የሱዳን የጦር ምርኮኞችን ረሽኗል በሚል በቀረበበት ክስ ምንም ተሳትፎ እንደሌለውም ተናግረዋል።
ይልቁንም መንግሥታቸው የሁለቱን አገሮች ጉዳይ በሰላም ለመፍታት አሁንም ቁርጠኛ መሆኑን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።