1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአሙሩ ወረዳ በታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት ሶስት ሰዎች ተገደሉ

ዓርብ፣ ግንቦት 30 2016

በሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ከትናንት በስቲያ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡ በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች በሞተር ሳይክል ወደ አጋምሳ ከተማ ሲጓዙ እንደነበር ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4gmzw
Äthiopien Oromia-Region West Shoa
ምስል Seyoum Getu/DW

በምስራቅ ወለጋ ዞን የታጣቂዎች ጥቃት እንደገና አገርሽቶ ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ

በአሙሩ ወረዳ በታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት ሶስት ሰዎች ተገደሉ 

በሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ከትናንት በስቲያ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡ በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች  በሞተር ሳይክል  ወደ አጋምሳ ከተማ ሲጓዙ እንደነበር ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡  በአሙሩ እና ምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ሀሮ በሚባል አዋሳኝ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ሲያደርሱ እንደነበር ነዋሪዎች ጠቁመዋል፡፡ ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወረው የታጣቂዎች ጥቃት ቀንሶ እንደነበር አመልክተዋል፡፡ በወረዳው ከ40 ሺ በላይ የተፈናቀሉ ሰዎች በቅርቡ ወደ ቤታቸው መመለሳቸው የተነገረው በዚሁ ሳምንት ነው፡፡

"አስቸኳይ መፍትሔ የሚሹ" የመብት ጥሰቶች

በአሙሩ ወረዳ በታጣቂዎች ጥቃት የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ

በአሙሩ ወረዳ ለ3 ዓመታት በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ከ40ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቅለው መቆየታቸውን እና በአሁኑ ወቅት ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን የወረዳው አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት በወረዳው ውስጥ የሚንቀሳቀሱ እና ድንበር ተሻግሮ ጥቃት የሚያደርሱ ታጣቂዎች ጥቃት አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ ከትናንት በስቲያ ከአሙሩ ወረዳ አጎራባች ከሆነው  የምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ አጋምሳ  ከተማ ሲያቀኑ የነበሩ ሶስት ሰዎች ላይ ሀሮ ተብሎ በሚታወቅ ቦታ ታጥቆ ይንቀሳቀሳሉ የተባሉና ጽንፈኛ ብሎ የጠሯአቸው ሀይሎች ጥቃቱን ማድረሳቸውን ነዋሪው አመልክተዋል፡፡

የምዕራብ ኦሮሚያ ገጠራማ አካባቢ
በአሙሩ ወረዳ ለ3 ዓመታት በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ከ40ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቅለው መቆየታቸውን እና በአሁኑ ወቅት ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን የወረዳው አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡ምስል Seyoum Getu/DW

‹‹ አንድ ሞተር  አጋምሳ ከተማ እየተመለሰች ባለችበት ሰዓት ነው ሀሮ የሚባል ቦታ እንዳለፉ ጎንኬ የሚባል ቦታ ላይ ታጣቂዎቹ ባደረሱት ጥቃት ህይወታቸው ያለፈው፡፡ ከሞቱት መካከል አንድ መምህር ይገኝበታል፡፡ ባጠቃላይ የሶስት ሰዎች ህይወት አልፈዋል፡፡ »

ከምስራቅ ወለጋ ዞን ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች እየተመለሱ ነው

በአሙሩ ወረዳ ነዋሪና ባለፈው ሳምንት አሙስ ከቆዩበት መጠለያ ጣቢያ ወደ ቀድሞ ቤታቸው መመለሳቸውን የነገሩን ሌላው ነዋሪም በወረዳው ለረጅም  ጊዜ የታጣቂዎች ጥቃት ቀንሶ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ከትናንት በስቲያ በታጣቂዎች ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎችም ያልታጠቁና ሠላማዊ ሰዎች እንደሆኑ አመልክተዋል፡፡ በጥቃቱ ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች ስርዓተ ቀብራቸው ትናንት መፈጸሙን ነዋሪው አክለዋል፡፡

በወለጋው ግጭት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች
በአሙሩ ወረዳ ለ3 ዓመታት በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ከ40ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቅለው መቆየታቸውን እና በአሁኑ ወቅት ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን የወረዳው አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡ምስል Alemnew Mekonnen/DW

በአሙሩ ወረዳ በሰላማዎ ሰዎች ላይ ደርሰዋል የተባለውን ጥቃት አስመልክቶ ማብራር የሰጡን የአሙሩ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ቂጠሳ በአሙሩወረዳና ኪረሙ ወረዳ መካከል በሚገኘው ጎንካ በሚባል ቦታ በደረሰው ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን አረጋግጠዋል፡፡ ‹‹  በሶስት ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሰዋል፡፡ ጎንካ ጫካ ውስጥ ጥቃት አድርሰው ሞተሩንም እዛው ጥለው የሄዱት፡፡ በአዋሳኝ አካባቢዎች እየገቡ ነው ጥቃት አድርሰው የሚመለሱት፣በጸጥታ ጉዳይ ኦፕሬሽን የሚፈልጉ ቦታዎች አሉ፡፡ እንደ አሙሩ በዚህ ጉዳ ላይ እየተሰራ ነው፡፡»

ኪራሙ ወረዳ ሰዎች ተገደሉ፣ ከብቶች ተዘረፉ

 በአካባቢው በተለያዩ ስም የምንቀሰቀሱ ታጣቂዎች ጥቃት እንደሚያደርሱ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ የአሙሩ ወረዳ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት ሰሞኑን በሰጡን ማብራሪያ በወረዳው አንጻራዊ ሠላም በመስፈኑ 45ሺ 915  የተፈናቀሉ ሰዎች  ወደ ቀያአቸው መመለሱን ገልጸዋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ታምራት ዲንሳ

ሸዋዬ ለገሰ