1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ሮሮ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 11 2015

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማህበር በአዲስ አበባ የ300 አባላቱ መሥሪያ ቦታዎች በመንግሥት እንዲፈርሱ በመደረጉ ለችግር መጋለጣቸውን ገለፀ። በአዲስ አበባ ከተማ ሸራ ወጥረው ይሠሩ የነበሩ አባላቱ ቦታቸው በመፍረሱ ለጎላ ችግር መጋለጣቸውን በመግለጽ መንግሥት መፍትሔ የማይሰጣቸው ከሆነ ጥያቄያቸውን በአደባባይ ሰልፍ እንደሚያቀርቡ ገልጿል።

https://p.dw.com/p/4VI9a
የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ ሸራ ወጥረው ይሠሩ የነበሩ አባላቱ ቦታቸው በመፍረሱ ለጎላ ችግር መጋለጣቸውን በመግለጽ መንግሥት መፍትሔ የማይሰጣቸው ከሆነ ጥያቄያቸውን በአደባባይ ሰልፍ እንደሚያቀርቡ ገልጿል። ፎቶ ማኅደር የኢትዮጵያ ካርታ

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማህበር በአዲስ አበባ የ 300 አባላቱ መሥሪያ ቦታዎች በመንግሥት እንዲፈርሱ በመደረጉ ለችግር መጋለጣቸውን ገለፀ። ማህበሩ በአዲስ አበባ ከተማ ሸራ ወጥረው ይሠሩ የነበሩ አባላቱ መሥሪያ ቦታቸው በመፍረሱለጎላ ችግር መጋለጣቸውን በመግለጽ መንግሥት መፍትሔ የማይሰጣቸው ከሆነ ጥያቄያቸውን በአደባባይ ሰልፍ እንደሚያቀርቡ ገልጿል። ማህበሩ ኢትዮጵያ ውስጥ እስከ 17 ሚሊየን የሚሆኑ አካል ጉዳተኛ እንዳሉ እና በማህበሩ ተመዝግበው አባል የሆኑት ከ17 ሺህ ናቸው ብሏል።

ከፍተኛ ቁጥር ያለው አበላትን ያቀፈው የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማህበር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ አበባን ውበት ቀንሷል፣ የከተማወን ገጽታ አበላሽቷል በሚል ሸራ ወጥረው ይሰሩ ከነበሩ በርካታ ዜጎች መካከል ሦስት መቶ ያህል አባሉ የሆኑ አካል ጉዳተኞች የመሥሪያ ቦታቸው ፈርሶ ለችግር ተዳርገዋል ብሏል።

የአካል ጉዳተኞች  ቀን በድሬዳዋ ከተማ፦ ፎቶ ከማኅደር
የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማህበር በአዲስ አበባ የ 300 አባላቱ መሥሪያ ቦታዎች በመንግሥት እንዲፈርሱ በመደረጉ ለችግር መጋለጣቸውን ገለፀ። የአካል ጉዳተኞች ቀን በድሬዳዋ ከተማ፦ ፎቶ ከማኅደርምስል Mesay Tekilu/DW

የማህበሩ ዋና ጸሐፊ አቶ አዲስ አለም በቀለ ይህንን ተከትሎ ብዙዎች አባሎቻቸው ለልመና ጎዳና እየወጡ መሆኑን ገልፀዋል። ችግራቸውን ለከንቲባ ጽ/ቤት በአካል በመሄድም ሆነ በደብዳቤ ደጋግመን አሳውቀናል የሚሉት ኃላፊው ጥረታቸው በጎ ምላሽ እንዳላገኘ ገልፀዋል።

ከአባሎቻቸው መካከል የተወሰኑት ተለዋጭ ቦታ እንዲያገኙ ቢደረግም የተሰጣቸው ቦታ ካለባቸው የአካል ጉዳት አንፃር ምቹ አለመሆኑን አስታውቀዋል። በቀጣይ ጥያቄያቸው በአግባቡ ምላሽ ካላገኘ ወደ አደባባይ እንደሚወጡና የተቃውሞ ድምፅ እንደሚያሰሙም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያውስጥ እስከ 17 ሚሊየን የሚሆኑ አካል ጉዳተኛ አሉ ያሉት አቶ አዲስዓለም በቀለ አዲስ አበባ ውስጥ በማህበሩ ተመዝግበው አባል የሆኑት 17 ሺህ መሆናቸውን ተናግረዋል። ይህ ቁጥር ግን ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ በጦርነት እና በሌሎች የፀጥታ ችግሮች ምክንያት የደረሰን የካል ጉዳት አያካትትም ብለዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ