በእስራኤል ፍልስጥኤም ግጭት ላይ የተሰበሰበው የአውሮጳ ሕብረት
ረቡዕ፣ ግንቦት 11 2013ማስታወቂያ
አስረኛ ቀኑን ባስቆጠረው የእስራኤል ፍልስጥኤም ግጭትን አስመልክቶ ትናንት ተሰባስበው የነበሩት የአውሮጳ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች የጋራ መግለጫ ሳያወጡ ስብሰባው ተጠናቋል። የሀማስን የሮኬት ጥቃት የሽብር የእስራኤልን የአየር ጥቃት ደግሞ ራስን መከላከል ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቹ እስራኤል የምትወስደው የአየርጥቃት ተመጣጣኝ እንዲሆን ጠይቀዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ሁለቱ ወገኖች አንዱ በሌላው ላይ የሚያደርሱት ጥቃት ቆሞ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ የህብረቱ ፍላጎት መሆኑን የህብረቱ የውች ጉዳይ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል ተናግረዋል።
ገበያው ንጉሴ
ታምራት ዲንሳ
ነጋሽ መሐመድ