1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኒጀር፤ ኤኮዋስ ወታደራዊ ኃይል እንደሚልክ አስታወቀ

ዓርብ፣ ነሐሴ 5 2015

በኒጀር የተካሄደውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ በተካሄደዉ ልዩ ጉባዔ ፤የምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት ኤኮኖሚ ማኅበረሰብ (ኢኮዋስ) አባል ሃገራት ለኒጀር ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዲፈለግ መጠየቃቸዉ ተነገረ። ከዚህ በተጨማሪ ኤኮዋስ ወታደራዊ ኃይሉን ወደ ኒጀር እንደሚልክም አስታዉቋል። የአፍሪቃ ህብረት የኤኮዋስን ዉሳኔ እንደሚደግፍ አስታዉቋል።

https://p.dw.com/p/4V5Bm
Äthiopien Hauptqartier der Afrikanischen Union in Addis Abeba
ምስል Solomon Muchie/DW

በኒጀር የተካሄደውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ በተካሄደዉ ልዩ ጉባዔ ፤የምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት ኤኮኖሚ ማኅበረሰብ (ኢኮዋስ) አባል ሃገራት ለኒጀር ዲፕሎማሲያዊየኒጀር ወታደራዊ ጁንታ የሀገሪቱን የአየር ክልል ዘጋ መፍትሄ እንዲፈለግ መጠየቃቸዉ ተነገረ። ከዚህ በተጨማሪ ኤኮዋስ ወታደራዊ ኃይሉን ወደ ኒጀር እንደሚልክም አስታዉቋል። ወደ ኒጀር የሚላከዉ ወታደራዊ ኃይል የሀገሪቱን "ህገ መንግስታዊ ስርዓት ማስመለስ አለበት" ሲሉ የምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት፤ ኦማር ቱሬ ተናግረዋል። «የመከላከያ ጉዳዮች ዋና መመሪያ ሰጭ ኮሚቴ፤ በአስቸኳይ የምዕራብ አፍሪቃ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ /ECOWAS/ ተጠባባቂ ሃይል እንዲሰማራ አዟል።ይህም የኒጀር ሪፐብሊክ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ ነው ።» የወቅቱ የኢኮዋስ ፕሬዚደንት ቦላ ቲኑቡ በበኩላቸዉ ለኒጀሩ ቀዉስ ዲፕሎማሲያዊ ድርድር ቅድሚያ መስጠት "ወሳኝ" ጉዳይ ነዉ ብለዋል።ኒዠር፦ የኢኮዋስ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ይሳካ ይሆን? የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩሉ በመፈንቅለ መንግሥት ከስልጣን የተባረዉ እስር ላይ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ባዙም "ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ" እንዲለቀቁ ሲል ጥሪ አቅርቧል።  የአፍሪቃ ህብረት የኤኮዋስን ዉሳኔ እንደሚደግፍ አስታዉቋል

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢኮዋስ ህገ- መንግስታዊ ስርዓትን ለማስመለስ በኒጀር፤ ወታደራዊ ጣልቃ ቢገባ አይቮሪ ኮስት ጦር ሰራዊት ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ዛሬ አስታወቀች።የኒዠር መፈንቅለ መንግስትና ማስጠንቀቂያዉ የአይቮሪ ኮስት ፕሬዚዳንት አላሳን ዋታራ ኤኮዋስ በኒጀር ስልጣኑን ይዘዉ በሚገኙት ወታደራዊ ኹንታ ላይ ለሚያካሂደዉ እርምጃ፤ አገራቸዉ አስፈላጊዉን ወጭ ሁሉ አዘጋጅታ በተጠንቀቅ መሆንዋን ገልፀዋል። እስካሁን ወደ ኒጀር ወታደሮችን ለመላክ ፍቃደኛ መሆናቸውን ከገለጹት የኢኮዋስ አባል ሃገራት መካከል ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል እና ቤኒን ይገኙበታል።

 

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ