1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«አስቸጋሪ ምርጫዎች» ድራማ፥ ክፍል 2

እሑድ፣ መጋቢት 6 2012

ይህ «አስቸጋሪ ምርጫዎች» በሚል ርዕስ የሚቀርብላችሁ የወንጀል ተፋላሚዎቹ ተከታታይ ድራማ ሁለተኛ ክፍል ነው።

https://p.dw.com/p/3ZTTx
DW Crime Fighters Serienmotiv „Uneasy choices“

«ተስፋችን ታድሷል»

ይህ «አስቸጋሪ ምርጫዎች» በሚል ርዕስ የሚቀርብላችሁ የወንጀል ተፋላሚዎቹ ተከታታይ ድራማ ሁለተኛ ክፍል ነው። ያለፈው ክፍል የተጠናቀቀው ከንቲባው ከአካባቢ እና ጤና ጥበቃ ቡድን አባላት ጋር ስብሰባቸውን በድንገት ሲዘጉ ነው። ታስታውሱ እንደሆን መንግስት የማጋሪያ ከተማ ለመጪው ዝናባማ ወቅት ራሷን እንድታዘጋጅ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል። ከተማዋም ከፍተኛ የጎርፍ አደጋንና ሌላ የኮሌራ ወረርሽኝን መከላከል እንዲቻል ገንዘቡን መሰረተ ልማት ላይ ለማዋል አስባለች። ይሁንና ይህ እስካሁን ተግባራዊ አልሆነም። ከንቲባው በዚህ ጉዳይ ላይ ሲጠየቁ ይባሱኑ አጠራጣሪ ምላሽ ነው የሚሰጡት።  «ተስፋችን ታድሷል» የተሰኘው የዛሬው ክፍል የሚጀምረው በአካባቢ እና ጤና ጥበቃው ቢሮ ውስጥ ነው። 

ደራሲ፦ ፒናዶ አዳማ ዋባ
አዘጋጅ፦ ማንተጋፍቶት ስለሺ