«አስቸጋሪ ምርጫዎች» ድራማ፥ ክፍል 4
እሑድ፣ መጋቢት 20 2012ማስታወቂያ
ባለፈው ጊዜ የሐይማኖት ወላጆች አቶ ባቢሌ እና ወይዘሮ አበበች ወደቤት ያልተመለሰች ልጃቸውን በሚመለከት አስደንጋጭ ዜና ሰምተው ነበር። ሐይማኖት በበጎ ፍቃደኝነት ለአካባቢ እና ጤና ጥበቃው ጽሕፈት ቤት ስትሠራ ነው የከረመችው። ኅብረተሰቡ በሙሉም ለመጪው የዝናብ ወቅት እየተዘጋጀ ነው። የጎርፍ መጥለቅለቅ ወይም ሌላ የኮሌራ ወረርሽኝ እንዳይከሰት ሰግቷል። ታድያ ሃይማኖት በሌለችበት ይህንን እንደምን ይወጡት ይኾን? የአካባቢ እና ጤና ጥበቃው ጽሕፈት ቤት በጉጉት ከመንግሥት ሲጠብቀው የነበረውን የርዳታ ገንዘብ አግኝቶ ይሆን? ሃይማኖት ከመሰወሯ በፊት ከንቲባው እና አለቃዋ አቶ አቡበክር ገንዘብ እንዴት አድርገው እንደሚያጭበረብሩ ሲዶልቱ ሰምታለች። “እውነታውን ፍለጋ” የተሰኘውን የዛሬውን ክፍል የምንጀምረው መርማሪ ፖሊሶቹ ወታደር ፋና እና ወታደር ክፍሌ የሃይማኖትን ጉዳይ ሲመረምሩ ነው።
ደራሲ፦ ፒናዶ አዳማ ዋባ
አዘጋጅ፦ ማንተጋፍቶት ስለሺ