1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አትሌቲክስ ስፖርት እና የእግር ኳስ ዘገባዎች

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 21 2017

28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መረጠ ። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን በመተካት ለቀጣይ 4 አመት ፌዴሬሽኑን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ሰህንን መምረጡ ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/4oh6p
Fußball Champions League 2024 | Liverpool vs. Leverkusen | Luis Diaz trifft für Liverpool
ምስል Carl Recine/Getty Images

የታህሳስ 21 ቀን 2017 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት

28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መረጠ 

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን  ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን በመተካት ለቀጣይ 4  አመት ፌዴሬሽኑን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ሰህንን መምረጡ ይታወሳል ።

ኮማንደር አትሌት ስለሺ በአቴንስ እና ቤጂንግ ኦሎምፒኮች በሄልሲንኪ እና ኦሳካ የአለም ሻምፒዮናዎች የብር ሜዳልያዎች ለሃገሩ ያስገኘ በፓሪስ አለም ሻምፒዮናም የነሀስ ሜዳልያ አቡጃ ላይ በተደረገው የአፍሪካ ጨዋታዎች በ10ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳልያ ለሀገሩ ያሰገኘ ብረቱ  አትሌት መሆኑ ይታወቃል።  ለሚቀጥሉት 4 አመታት ከፍተኛ ውዝግብ የሚነሳበትን የኢትዮጵያ አሌቲክሰ ፊዴሬሽንን ለመምራት የተቀበለው አዲሱ አመራር መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ  የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መርጧል።

– የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት አድርጎ መርጠዋል። ይህ አዲሰ የተመረጠው ሰራ አሰፈፃሚ ኮሚቲ በርግጥ በርካታ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ሲያሰተናግድ የከረመውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን  ወደፊት ለማራመድ ብቃት ያለው ነው ሲል ለDW የተናገረው ጋዜጠኛ ምሰጋናው ታደሰ ነው ።

ከዚሁ ከ ሀገር ውሰጥ የአትሌቲክሰ ዜና ሳንወጣ 

የአጭር፣ መካከለኛ ፣ 3 ሺህ ሜትር መሰናክል፣ የሜዳ ተግባራት እና የእርምጃ ውድድሮች በያዝነው ወር ይካሄዳሉ

ኢትዮጵያውያን ያሸነፉባቸው የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች እና የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ፍጻሜ

የኢትዮጵያ የአጭር፣ እና መካከለኛ እርቀት ፣ 3 ሺህ ሜትር መሰናክል፣ እና የእርምጃ ውድድሮች ከነገ ታሕሣሥ 22 እስከ 26 እንደሚካሄደ‍እ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ ።

በውድድሩ 21 ክለቦች፣ ሁለት ማሰልጠኛ ተቋማት እና አንድ አካዳሚን ጨምሮ 24 ተቋማት ይካፈላሉ ።በዚህ ውድድር በሴቶቹ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣ ወርቅነሽ መለሰ፣ አክሱማዊት አምባዬ፣ ሳሮን በርሄ፣ ነፃነት ታደሰ እና ፍሬሕይወት ገሰሰ እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡፡

የታላቁ የቦቆጂ ሩጫ
የኢትዮጵያ የአጭር፣ እና መካከለኛ እርቀት ፣ 3 ሺህ ሜትር መሰናክል፣ እና የእርምጃ ውድድሮች ከነገ ታሕሣሥ 22 እስከ 26 እንደሚካሄደ‍እ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ ።ምስል Omna Tadel

በወንዶቹ ደግሞ አትሌት ታደሰ ለሚ፣ ጌትነት ዋለ፣ አብርሃም ስሜ፣ ሳሙኤል ፍሬው፣ መዝገቡ ስሜ፣ መለስ ንብረት እና አድሐና ካህሳይ ከሚሳተፉ አትሌቶች መካከል መሆናቸውን ፊዲሬሸኑ። አሰታውቆዋል 

የኢትዮጵያ እግርኳስ  ዋንጫ ጨዋታዎች

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሀገሪቱን የዋንጫ ጨዋታዎች ለተመልካች ክፍት እንዲሆኑ መወሰኑን አስታውቆዋል ተጋጣሚ ክለቦች ደጋፊዎቻቸው ስፖርታዊ ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ ክለባቸውን እንዲደግፉ የማስተባበር ስራ እንዲሰሩ እና ክለቦችም ለስፖርታዊ ጨዋነት ቅድሚያ ሰጥተው ኃላፊነት መውሰድ እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡

ፌዴሬሽኑም የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት በሚፈፅሙ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት እና ማርኬቲንግ ዳይሪክተር አቶ አብርሀም ገ/ማሪያም ለሰፖረታዎ ጨዋነት ክለቦች ለደጋፊዎቻቸው ድርጊት ሀላፊነቱን ይወሰዳሉ ሲሉ ለ   Dw ተናግረዋል 

የኢትዮጵያውያን አትሌቶች አንጸባራቂ ድል እና የአፍሪቃ ዋንጫ ፍጻሜ

 

የውጭ 

ቡንደስሊጋ፣ ላ ሊጋ እና የተቀሩት ውድድሮች በክረምት ዕረፍት ላይ እያሉ እረፈት ለምኔ ያለው  የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አስደሳች  የበአል ወቅት ውድድሮችን በማድረግ የአለም ምርጥ የእግረኩዋሰ ፈልሚያ መንደር የሚለዉን ዝና አሰጠብቆ ሰንብቶዋል 

ሊቨርፑል መሪነቱን አጠናክሯል
ሊቨርፑል ሁለት አስደናቂ ድሎች ተጎነፅፎዋል ምስል Molly Darlington/REUTERS

ሊቨርፑል ሁለት አስደናቂ ድሎች ተጎነፅፎዋል አርብ እነሱ በቦክስንግ ዴይ በሚሉት ቀን ሌስተር ሲቲን 3-1 በማሸነፍ የጀመረዉ የሊጉ መሪ  በመቀጠል ትላንት እሁድ ዌስት ሃም ዩናይትድን5-ለ0 በማሸነፍ ጨዋታውን አጠናቀዋል። 

ይህም በሊጉ አንደኛደረጃ ላይ ያላቸውን መሪነት ወደ ስምንት ነጥብ አሳድጓል።ሳላህ በሁለቱም ጨዋታዎች ጎሎችን በማስቆጠር ለቡድኑያለዉን አስፈላጊነት አስመሰክሮዋል 

ማንቸስተር ሲቲ በአንፃሩ ከፍ ዝቅ ያለበት ሳመንትአሳልፏል። ሀሙስ በሜዳቸዉ ከኤቨርተን ጋር ባደረገው ጨዋታ  1-1  ተለያይቶ ነጥብ ተጋርቶ ቢወጣም   ሲቲ እሁድ ሌስተር ሲቲን 2-ለ0 በማሸነፍ ለአምስት ተከታታይ ጨዋታወች የራቀውን አሽናፊነት አግኝተዋል ፤

 የኢትዮጵያ እግር ኳስን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጨዋቾች ይታደጉ ይሆን?

ነቲንግሃም ፎረስት ኢቨርተንን 2-ለ0 በማሸነፍ አስደናቂውጤት አስመዝግቧል በልተጠበቀ ሁኔታ የሊጉ ቶፎካካሪ የሆነዉ ነቲነግሃም ፎሬስት ይህ ውጤት በሊጉ ሁለተኛ ደረጃላይ እንዲቀመጥ አሰችሎታል 

በሌላ በኩል ቼልሲ በቦክስንግ ዴይ ከፉልሃም ጋር ባደረገውጨዋታ 2-ለ1 ተሸንፏል። ኮል ፓልመር የመጀመሪያውን ግብቢያስቆጥርም ሃሪ ዊልሰን እና ሮድሪጎ ሙኒዝ በመጨረሻውደቂቃ ላይ ጎሎችን አስቆጥረዉ ፉልሃምን አሽናፊአድርገዉታል ፤ ይህም በስታምፎርድ ብሪጅ የነበሩትንደጋፊዎችን ያሳዘነ ነበር።

አርነ ስሎት አሰልጣኝ
ሊቨርፑል መሪነቱን አረጋግጧልምስል Propaganda Photo/Imago Images

ቡንደስ ሊጋ፣ እና ይ ላ ሊጋ  ዕረፍት ላይ ስለነበሩ ምንም ጨዋታዎች  አለመካሂዳቸው  

የእንግሊዘ‍ዝ ፕሪምየር ሊግ። ድንቅ ዉጤቶችን ፣ አስገራሚ ሽንፈቶችን እናጎልተው የሚታዩ አፈጻጸሞችን በማሳየት በበዓል ወቅት ለዓለምአቀፍ ደጋፊዎች ተመራጭ ሆኖ እንዲቆይ አድርጎታል።

ሊቨርፑል በጠንካራ ብቃት የሊጉ መሪ በመሆን የስምንት ነጥብ ልዩነት ይዞ አዲሱን አመት ሲቀበል ማንም ያልጠበቀዉ ነቲነገሃም ፎረስት ሁለተኛ የፊታችን ሮብ ከብሬንት ፎርድ ጋር ከባድ ፍልሚያ የሚጠብቀዉ አርሰናል ሶስተኛ ሆነዉ ይከተላሉ።

ሃና ደምሴ

ታምራት ዲንሳ