1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሕግ እና ፍትሕአፍሪቃ

አንድ ለአንድ፤ ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 18 2017

የሕግ ባለሙያ ናቸው። በኢትዮጵያ ታሪክም የመጀመሪያዋ ሴት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት በመሆን አገልግለዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ከሴቶች መብት ጋር በተገናኘ ከሚነሱት ግንባር ቀደም የሴቶች መብት ተቆርቋሪዎችም አንዷ ናቸው።

https://p.dw.com/p/4od4d
መዓዛ አሸናፊ
ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ሆነው በተሾሙበት ወቅት ፎቶ ከማኅደርምስል picture-alliance/Geisler-Fotopress/C. Niehaus

አንድ ለአንድ፤ ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ

 ለዚህም እሳቸውን ከሚመስሉ የሕግ ባለሙያ ሴት ባልደረቦቻቸው ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶችን ማሕበር በእንግሊዝኛ ምህጻሩ (EWLA)ን በመመሥረት ለዓመታት ማሕበሩን በፕሬዝደንትነት አገልግለዋል፤ መርተዋል። ከ30 ዓመታት በላይ የዘለቀው እሳቸው ከባልደረቦቻቸው ጋር ያቋቋሙት ይህ ማሕበር ከ130 ሺህ በላይ የጾታዊ ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሴቶችን በሙያው የረዳና የደገፈ ለመሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ። በዚህ ማሕበር ሥር የተሰባሰቡት የሕግ ባለሙያ ሴቶች ባደረጉት ያላሰለሰ ጥረትምየኢትዮጵያ የቤተሰብ ሕግ መሻሻሉም በታሪክነት ተመዝግቧል። ይህን የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማሕበር በፕሬዝደንትነት ያገለገሉት ክብር ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ለበርካታ ሴቶች ድጋፍ በማድረግ በንግድ ሥራ እንዲሰማሩ በማድረግ ላይ የሚገኘው የእናት ባንክም መሥራች ናቸው። በዚህ ብቻ ሳይወሰኑም በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትም በሙያቸውን አገልግለዋል። ዛሬም ልምድ ተሞክሯቸውን በተለያዩ ሃገራት ዩኑቨርሲቲዎች እየተገኙ ያካፍላሉ።

 ሸዋዬ ለገሠ ከክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ጋር ያደረገችውን ሙሉውን ቃለመጠይቅ ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ሸዋዬ ለገሠ