አደገኛው የኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰት
እሑድ፣ ሚያዝያ 13 2016በቅርቡ 170 ኢትዮጵያውያን ወደ የመን ለመሻገር ጀልባ ሲሳፈሩ ሶማሌላንድ ላይ ተይዘዋል። ባለፈው ሳምንት ወደ ሳዑዲ አረብያ ለመሄድ ጉዞ የጀመሩ 38 ኢትዮጵያውያን ጅቡቲ ድንበር አቅራቢያ የተጫኑበት ጀልባ ሰጥሞ ሞተዋል። በዚሁ ሳምንት ሳዑዲ አረብያ ውስጥ ችግር ላይ የወደቁ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ጥረት ቀጥሏል። የኢትዮጵያ መንግሥት በመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራትና በተለያዩ የአፍሪቃ ሀገራት እሥርን ጨምሮ በተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ የጀመረው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ነው።
የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሰቆቃ በሳዑዲ እስር ቤቶች ከየሀገራቱ መንግሥታት ጋር በሚደረግ ስምምነት ኢትዮጵያውያን በሕጋዊ መንገድ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት እንዲሄዱ በተጀመረ አሰራር ፍልሰተኞች የሚገጥማቸውን ችግር ለመቀነስ እየጣረ መሆኑንም ይናገራል። ይሁንና ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኃላ ዳግም በተመሳሳዩ አደገኛ ጉዞ እየፈለሱ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሀገራትና ወደ ደቡብ አፍሪቃ ለመግባት የሚሞክሩ ጥቂት አይባሉም። መደበኛ ያልሆነ በሚባለው በዚህ መንገድ በሚካሄደው ፍልሰት ሞትና እንግልትም አሁንም እንደቀጠለ ነው። የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ይዞታ
አደገኛው የኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰት የዛሬው እንወያይ ትኩረት ነው። በዚህ ውይይት ላይ የሚሳተፉ አራት እንግዶች ጋብዘናልበማላዊ የኢትዮጵያውያን ስደተኞች አበሳ እነርሱም ደረጀ ተግይበሉ በኢትዮጵያ ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከልና የተመላሽ ዜጎች ድጋፍና ክትትል መሪ አስፈጻሚ ፣አቶ ኮስሞስ ገብረ ሚካኤል በደቡብ አፍሪቃ ለኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሕግ ማማከር አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት ባለቤት አቶ ነብዩ ሲራክ ለብዙ ዓመታት ሳዑዲ አረብያ የኖረ የቀድሞ የዶቼቬለ ዘጋቢ እንዲሁም ወይዘሮ አዚዛ አሊ በአንድ የሳዑዲ ስራና ሰራተኛ አገናኝ ድርጅት በአስተርጓሚነት የሚሰሩ ኢትዮጵያዊት በጉዳዩ ላይ ተወያይተዋል።
ኂሩት መለሰ