1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከ-«በማድመጥ መማር ጀርባ» ያሉ ገፅታዎች

ሐሙስ፣ ጥቅምት 27 2001

የተዋጣላቸዉ ዘጋቢዎች፥ታታሪ፥ ወጣት የራዲዮ ጋዜጠኞች እና ድራማ ፀሐፊዎች ናቸዉ።ለራዲዮና ለአፍሪቃ ያላቸዉ ዉዴታ ያስተሳስራቸዋል

https://p.dw.com/p/Fods
ዘይነብ አዚዝ ሳሊም፥-ሥለ ልጃገረዶች የሚያወሳዉ ተከታታይ ዝግጅት ደራሲምስል DW

ከ-«በማድመጥ መማር ጀርባ» ያሉ ገፅታዎች

ከመላዉ አፍሪቃ ነዉ የተዉጣጡት።የተዋጣላቸዉ ዘጋቢዎች፥ታታሪ፥ ወጣት የራዲዮ ጋዜጠኞች እና ድራማ ፀሐፊዎች ናቸዉ።ለራዲዮና ለአፍሪቃ ያላቸዉ ዉዴታ ያስተሳስራቸዋል።ከእነዚሕ ከ-«በማድመጥ መማር» ጀርባ ያሉ ሰዎችን ከፊሉን እናስተዋዉቃችሁ።

ሆፕ አዚዳ ፥-መረጃን ከመዝናኛ ጋር በማቀናጀቱ ረገድ ልዩ ባለሙያ ናት።የሩዋንዳ ተወላጅ ናት።መሠረታዊ ማሕበራዊ ጉዳዮችን የሚዳስሱ በርካታ ድራማዎችን ፅፋለች።አዘጋጅታለችም።ከዚሕም በተጨማሪ መያዶችንና የመንግሥት ድርጅቶችን ታማክራለች።ከማከሬሬ ዩኒቨርስቲ በሙዚቃ፥ በዳንስና በድራማ ትምሕርት በማስተርስ ዲግሪ ተመርቃለች።

ጁስቲን ቢታጎዬ፥-የሙያ ጉዟዋን በትዉልድ ሐገሯ ብሩንዲ በጋዜጠኝነትና በቴሊቪዥን ዝግጅት አቅራቢነት አንድ አለች።ኑሯቸዉ ከአንድ የቁሻሻ ክምር ጋር ሥለተቆራኘ ሕፃናት የሚተርከዉን «Mieux vaut mal vivre que mourir» የተሰኘዉን የመጀመሪያ ዘጋቢ ፊልሟን FESPACO በሚል ምሕፃረ-ቃል በሚታወቀዉ የመላዉ አፍሪቃ የፊልም ትርዒት ላይ ሥታቀርብ፥ለሙያዉ ያላትን ዝንባሌና ፍላጎት አስመሰከረች።እንደ ሆፕ ሁሉ ካምፕላ ከሚገኘዉ ከማከሬሬ ዩኒቨርስቲ የማስተርስ ዲግሪ አላት።ለ «በማድመጥ መማር» ዝግጅት ግሎባላይዜሽን የተሰኘዉ አለም አቀፋዊ የምጣኔ-ሐብት ትስስር ሥለሚያሳድረዉ ተፅዕኖ ትዘግባለች።


ክርስቲነ ሐርየስ፥-ጀርመናዊ ናት።አለምን የማየት ጉጉቷን ለማርካት ሰሜናዊ ጀርመን የሚገኘዉን የትዉልድ መንደሯን ለቅቃ ለመጓዝ ሁል ጊዜ እንደተመኘች ነዉ።በዚሕ ሒደት ባንዲት አሐጉር «ፍቅር» ተለከፈች።በአፍሪቃ! ለዶቼ ቬለ ራዲዮ ከዩጋንዳ፥ ከኬንያ፥ ከሩዋንዳና ከቡርኪናፋሶ ሥትዘግብ ቆይታለች።ባሁኑ ወቅት የ«በማድመጥ መማር» ፕሮጀክት ሐላፊናት።

ሳም ቶሉሎፔ ኦሉኮያ፥-በሐገሩ ናይጄሪያ እዉቅ የራዲዮ፥ የቴሌቪዥንና የሕትመት ጋዜጠኛ ነዉ።ሞቅ ደመቅ ካለችዉ ከሌጎስ ከተማ ይዘግባል።በተለያዩ ጊዚያት ባሰራጫቸዉ ሳቢ ዘገባዎቹ የተለያዩ ሽልማቶችን አግኝቷል።ከተሰጡት በርካታ ሽልማቶች መካካል «የአመቱ ምርጥ የወንጀል ጉዳይ ዘጋቢ» እና «የአመቱ ምርጥ የራዲዮ ዘጋቢ» የሚሉት ይገኙበታል። ለ «በማድመጥ መማር» ከሚሰሩ የተዋጣላችዉ ወጣት ባለሙያዎች ጋር ተዋዉቋል።ሳም ወጣት አፍሪቃዉያን የተሻለ ሥራ እንዲያገኙ ያበረታታል።