በርካቶች ተፈናቅለዋል
ረቡዕ፣ መስከረም 3 2010ማስታወቂያ
በሶማሌ እና በኦሮምያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት መንስኤ ሰዎች መፈናቀላቸው ተሰማ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ከአካባቢው ነዋሪዎች እንደሰማው የተፈናቀሉት ቁጥር ከ1 ሺህ ሊበልጥ ይችላል። በግጭቱ መንስኤ በቀጠለው ተቃውሞም ዛሬ ከድሬዳዋ ከሐረር እና ጅግጅጋ ይነሱ የነበሩ አገር አቋራጭ አውቶብሶች እና ሚኒባሶች አገልግሎት አቋርጠዋል። ከድሬዳዋ እስከ ጅግጅጋ ያለው መንገድም ተዘግቷል። የአዲስ አበባውን ዘጋቢያችንን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔርን ኂሩት መለሰ አነጋግራዋለች። ዮሐንስ በቅድሚያ ትናንት እና ዛሬ በየከተሞቹ ስለሆነው የሰማውን ይገልጽልናል።
ዮሐንስ ገብረ ዝግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ