1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከእናቶቻቸው ጋር የሚታሰሩ ሕጻናት አያያዝ “አሳሳቢ” እንደሆነ ኢሰመኮ አስታወቀ

ቅዳሜ፣ መስከረም 26 2016

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን “በወንጀል የተጠረጠሩ ወይም የተከሰሱ ሕፃናት አያያዝ በማንኛውም ሁኔታ እና ወቅት ዓለም አቀፍና ሕገ መንግሥታዊ መስፈርቶችን በማሟላት እንዲተገበሩ” ጥሪ አቀረበ። ኮሚሽኑ “ከእስረኛ እናታቸው ጋር ማረሚያ ቤት ለሚቆዩ ሕፃናት አማራጭ የእንክብካቤ ማዕቀፍ” ሊመቻች እንደሚገባ ማሳሰቢያ ሰጥቷል

https://p.dw.com/p/4XFA3
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን
ከእናቶቻቸው ጋር የሚታሰሩ ሕጻናት አያያዝ “አሳሳቢ” እንደሆነ ኢሰመኮ አስታወቀምስል Ethiopian Human Rights Commission

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርት

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው ባለ 36 ገጽ የምርመራ ሪፖሪት አሳሳቢ ያላቸውን የመብት ጉዳዮች ዘርዝሯል። ከጥቃት የመጠበቅ መብት፣ በሴቶችና ሕፃናት መነገድ፣ ጠለፋ፣ አስገድዶ መድፈር እና መሰል ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች አሳሳቢ ችግሮች መሆናቸውን ጠቅሷል።

«የታራሚዎች በተጨናነቀ ሁኔታ መያዝ አሳሳቢ ነው»ኢሰመኮ

በኢሰመኮ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋርያት ይሁን ጨማሪ  ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ኢሰመኮ ግጭት የሚያስከትለው አደጋ እንዲሁም ሕፃናት እና ሴቶች በሀገር ውስጥ በሰው በመነገድ ድርጊት ሰብዓዊ ክብራቸው እየተገፈፈ መሆኑ ሌላው አሳሳቢ ችግር መሆኑን ጠቅሷል። ድርጊቱ አሳሳቢ የመብት ጥሰትን እያስከተለ ቢሆንም መንግሥት በሰው መነገድን በመከላከል ፣ በመቆጣጠር  እና ውጤታማ መፍትሔ በመስጠት ረገድ ተገቢውን ቦታ ያልሰጠው በመሆኑ ጉዳዩ እንዳሰሰበው በመግለጫው ጠቅሷል። 

የአማራ ክልል የጸጥታ ሁኔታ፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተፋላሚ ኃይሎች ወደ ውይይት እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢሰመኮ የሴቶች.እና የሕፃናት መብቶች ኮሚሽነር መስከረም ገስጥ ሕፃናትና ሴቶች ሰብአዊ መብቶቻቸው ተከብረው ከጥቃት፣ ከሥጋትና ከመድልዎ ነጻ የሆነ፤ ሰላም፣ እኩልነትና ሰብአዊ ክብር የሰፈነበት ሕይወትን እንዲኖሩ በሪፖርቱ የተካተቱትን ምክረ ሐሳቦች ለማስፈጸም ጥረት እና ርብርብ ሊደረግ ይገባል ብለዋል።

ሰለሞን ሙጬ
እሸቴ በቀለ