1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከጊምቢ ወረዳ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያአቸው እየተመለሱ ነው መባሉ

ዓርብ፣ የካቲት 15 2016

ከምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ተፈናለቅለው በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ አርቡ የቆዩ ዜጎች ወደ ቀያአቸው መመለስ ጀምረዋል፡፡ በትናትናው ዕለት በአማራ ክልል አራቡ እና ጃራ መጠለያ ከነበሩት መካከል 315 የሚደርሱት በመጀመሪያ ዙር ወደ ጊምቢ ወረዳ መመለሳቸውን የዞኑ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

https://p.dw.com/p/4cnj6
የምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ተፈናቃዮች መመለስ
የምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ተፈናቃዮች መመለስምስል Negassa Desalegn/DW

ጊምቢ ወረዳ በደረሰዉ ጥቃት በበሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝና አማራ ክልል ሸሽተው ቆይተዋል

ከጊምቢ ወረዳ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያአቸው እየተመለሱ ነው

ከምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ተፈናለቅለው በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ አርቡ የቆዩ ዜጎች ወደ ቀያአቸው መመለስ ጀምረዋል፡፡ በትናትናው ዕለት በአማራ ክልል አራቡ እና ጃራ መጠለያ ከነበሩት መካከል 315 የሚደርሱት በመጀመሪያ ዙር ወደ ጊምቢ ወረዳ መመለሳቸውን የዞኑ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ ትናንት አራት ሰዓት ገደማ ወደ ጊምቢ መመለሳቸውን ያነጋርናቸው ነዋሪዎችም ተናግረዋል።

በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም በጊምቢ ወረዳ ቶሌ በሚትባል አካባቢ ጥቃት መድረሱን ተከትሎበበሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝና አማራ ክልል ሸሽተው ቆይተዋል፡፡ ከጊምቢ ወረዳ ተፈናቅለው አማራ ክልል ከቆዩ መካከል የተወሰኑት ወደ ቀድሞ ቀያቸው እየተመለሱ እንደሚገኙ ተነግረዋል፡፡ በትናትናው ዕለት ከ3 መቶ በላይ ሰዎች ወደ አካባቢአቸው መመለሳቸውን አቶ ኢስማኤል ያሲን የተባሉ ነዋሪ ገልጸዋል፡፡ የነዋሪው ንብረት በመውደሙ ጨቆርሳ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በተዘጋጀው መጠለያ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

በደቡብ ወሎ ሐርቡ ከአንድ ዓመት ከ9 ወራት ቆይታ በኃላ የተመለሱት ሌላቸው ነዋሪም በትናትናው ዕለት ወደ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በመጀመሪያ ዙር በአምስት ተሽከራካሪ የተፈናቀሉ ዜጎች መመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡ በአካባቢው በ2014 ዓ.ም በደረሰው ጥቃት መኖሪያ ቤትና ሌሎች ንብረቶች በብዛት መውደማቸውን አመልክተዋል፡፡ ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ የወደመባቸው ነዋሪዎች ጊዜያዊ ቤቶች እየተዘጋጀ እንደሚገኝና በከፊል የወደሙ ቤቶች ደግሞ መጠገናቸውን ተናግረዋል፡፡

3 መቶ 15 ሰዎች በትናትው ዕለት ተመልሰዋል

የምዕራብ ወለጋ ዞን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት/ቡሳ ጎኖፋ ኃላፊ ወ/ሮ ነጸነት አለማየሁ የተፈናቀሉ ዜጎች እየተመለሱ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ በጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ የተጎዱ 90 የሚደርሱ ቤቶች መጠገናቸውን አብራርተዋል፡፡ አርሶ አደሩ ወደ ምርት እስኪገባ ድረስ ሰብአዊ ድጋፍ ለተመለሱ ዜጎች እንደሚቀርብም ተናግረዋል፡፡

የምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ተፈናቃዮች መመለስ
የምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ተፈናቃዮች መመለስምስል Negassa Desalegn/DW

‹‹ የተመለሱ ሰዎች 315 በተሰብ ናቸው፡፡ ትናንት ጠዋት ነው ወደ ቶሌ የገቡት፡፡ እንደ አተቃላይ ከ1ሺ በላ ሰዎች ይመጣሉ ብለን ነበር፡፡ 221 አባዎራዎች ባጠቃላይ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡‹‹

በጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በሰኔ 2014 በደረሰው ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት ማለፉን በወቅቱ መንግስት ይፋ አድርገዋል፡፡ በተመሳሳይ በምስራቅ ወለጋ ሲቡ ስረ እና ጎቡ ሳዩ ከተባሉ ወረዳዎች ተፈናቅለው ወደ አማራ ክልል ሸሽተው የነበሩ ዜጎች እየተመለሱ እንደሚገኙ የዞኑ ቡሳ ጎኖፋ ጽ/ቤት ወይም የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ