1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወደ ቀኝ ያዘነበለዉ የ2024 የአውሮጳ ፓርላማ ምርጫ ዉጤት

ሰኞ፣ ሰኔ 3 2016

በ27ቱ የህብረቱ አገሮች የተካሄደው የፓርላማ ምርጫ ብዙዎች እንደገመቱት የቀኝና ግራ አክራሪ ፓርቲዎች ተጠናክረው የወጡበት ነዉ። የአረንጓዴዎቹና ሊበራሎቹ ፓርቲዎች በርካታ መቀመጫችዎቻቸውን ያጡበትም ነዉ። የሶሻል ዲሞክራቶቹ ቡድኖች ከሞላ ጎደል በነበረው የቀጠሉበትና የመሀል ቀኙ የአውሮጳ ህዝቦች ፓርቲ የፓርላማውን 189 መቀመጫዎች አግኝተዋል።

https://p.dw.com/p/4gsVM
ወደ ቀኝ ያዘነበለዉ የ2024 የአውሮጳ ፓርላማ ምርጫ ዉጤት
ወደ ቀኝ ያዘነበለዉ የ2024 የአውሮጳ ፓርላማ ምርጫ ዉጤትምስል Dwi Anoraganingrum/Panama Pictures/IMAGO

የ2024 የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ ዉጤት

የ2024 የአውሮጳ ፓርላማ ምርጫ ዉጤት
ባለፉት አራት ቀናት በ27ቱ የህብረቱ አገሮች የተካሄደው የአውሮጳ ፓርላማ ምርጫ ብዙዎች እንደገመቱት የቀኝና ግራ አክራሪ ፓርቲዎች ተጠናክረው የወጡበት፤ የአረንጓዴዎቹና ሊበራሎቹ ፓርቲዎች በርካታ መቀመጫችዎቻቸውን ያጡበት፤ የሶሻል ዲሞክራቶቹ ቡድኖች ከሞላ ጎደል በነበረው የቀጠሉበትና  የመሀል ቀኙ የአውሮጳ ህዝቦች ፓርቲ (ኢፒፒ) ግን  ከ720 የፓርላማው መቀመጫዎች 189 ወንበሮችን በማግኘት ትልቁ ፓርቲ በመሆን የዘለቀበት ሆንዋል። የመሀል ቀኙ ኢፒፒ ትልቁ ፓርቲ መሆን፤ የፓርቲውን እጩ የኮሚሽን ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ፎን ደር ላይየን የሁለተኛ የፕሬዚዳንትነት ዘመን የሚያረጋግጥ ሆኖ ተወስዷል። በአሁኑ ወቅትም የመሀል ቀኝና ግራ ፓርቲዎች ነባር ጥምረቶች ከሊበራሎቹ ጋር ሆነው የህብረቱን ፖሊስዎችና እቅዶች ሊያስቀጥሉ እንደሚችሉ በሰፊው እየተነገረ ነው።  ወይዘሮ ፎን ደር ላየን በቀጣይም የኮሚሽኑ ፕሬዚድንት እንዲሆኑ እጩ አድርጎ ያቀረባቸው የአውሮጳ ህዝቦች ፓርቲ ትልቁ ፓርቲ ሆኖ መውጣቱን ትከትሎ ባሰሙት ነግግር፤ አሸናፊነቱ ከትልቅ ሀልፊነት ጋር የመጣ መሆኑን አጽናኦት ስተው ተናግረዋል፤ “ ዛሬ ለአውሮጳ ህዝቦች ፓርቲ ትልቅ ቀን ነው፡፤ መህሉ ተጠናክሮ ወቷል፤ ግን ደግሞ ያክራሪ ሀሎች ከግርራ ቀኝ  እያደጉና እየተስፋፉ መምጣታቸው ገሀድ ነው” በማለት የተገኘው ድል  ተጨማሪ ሀላፊነትንም ይዞ የመጣ መሆኑን አስገንዝበዋል።


ምርጫው የተካሄደበት አክባቢያዊና አለማቀፋዊ ድባብ 

 
ወይዘሮ ፎንዴርሌየን ይህ ምርጫ የተካሄደውና ውጤትም የተገኘው በተለየ አለማቀፋዊና አካባቢያው  ድባብ ውስጥ ተሁኖ እንደሆነም አስታውሰዋል፤ “ ይህ ምርጫ እንዲሁ  የተካሄድ አይደለም ። አለማችን በቀውስ ውስጥ ነው ያለችው። የውጭና የውስጥ ሀይሎች ማህበረሳሰባችንን ሊያናጉና የአውሮጳ ህብረትንም ለማዳከም ጥረት ያደርጋሉ። ይህ ግን እንዲሆን ከቶም ቢሆን አንፈቅድም በማለት ለአፍቃሪ የአውሮጳ ህብረት ኃይሎች ያአንድነት ጥሪ አቅርበዋል።

Europawahl Berlin Afd Wahlparty
የምርጫ ስኬት፤ የ AfD ተባባሪ ሊቀመንበር አሊስ ቫይደል እና ቲኖ ቹርፓላምስል FILIP SINGER/EPA


ብሔረተኛና አክራሪ ፓርቲዎች በተለይ ጎልተው የወጡባቸው አገሮች


በዚህ ምርጫ የአክራሪ ብሂረተኞች ጎልተው ክወጡባቸው በዋናነት የሚጠቀሱት ጀርመንና ፈርነሳይ ናቸው፡ በተለይ በፈረንሳይ የወይዘሮ  ማሪ ሌፔን አክራሪ ብሔረተኛ ፓርቲ የገዥውን የፕሬዝዳንት ማክሮን ፓርቲ በእጥፍ በመብለጥ አሸናፊ ሆኖ በመውጣቱ ፕሬዚዳንት ማክሮ ፓርላማቸውን በትነው ምርጫ እዲጠሩ አስገድዷቸዋል።” ዛሬ ፓርላማው እንዲበተን አዝዣለሁ። ውሳኔው ከባድ ነው፤ ይሁን እንጂ ያገሪቱን ሉላዊነትና መጻኢ ዕድል በሚመለከት ዜጎች እራሳቸው እንዲወስኑ በማስፈልጉና በዴሞክራሲያችንም ስለማምን ይህን ውሳኔ መወሰን አስፈልጓል” በማለት ከዚህ ሌላ እሳቸው እንዳሉት በፈረንሳይ ዴሞክርሲ ላይ ያንሻበበውን አደጋ ለመቀልበስ ያሚያስችል ስልት አለመኖሩን አስታውቀዋዋል። ምርጫውም በዚህ ወር መጨረሻ እንደሚክሄድ ተገልጿል ። ይህ ይልተጠበቀ የፕሬዝዳንቱ ውሳኔ  ማክሮን ያጡትን ድጋፍ  መልሶ የሚያስገኛቸው ይሆን ወይንስ ጭራሹን ከመንበረ ስልጣናቸው የሚያወርዳቸው ይሆን? ብዙዎች ከውዲሁ እየጠየቁት ያለ  ጥያቄ ነው፤።
የምርጫው ውጤት የቤልጀየምን ጠቅላይ ሚኒስተርንም አስነስቷል። 

የአዉሮጳ ፓርላማ ምርጫ 2024
የአዉሮጳ ፓርላማ ምርጫ 2024ምስል Geert Vanden Wijngaert/AP/dpa/picture alliance


ይህ ምርጫ የቤጅየየም ጠቅላይ ሚኒስተር ሚስተር አሌክሳደር ዴክሮንም ከስልጣናቸው አንዲወርዱ አድርጓል። በቤልጅየም የተካሄደው መርጫ የአውሮጳ ፓርላማ ምርጫ ብቻ ሳይሆን የፌዴራልና የአካባቢም ሲሆን፤ አሸናፊ ሆነው የወጡት የቀኝና ተገንጣይ ፓርቲዎች ናቸው።፡ የጠቅላይ ሚኒስተር ዴክሮን የሊበራል ፓርቲ ግን በክፍተኛ ደረጃ በመሸነፉ ነው ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ያስታወቁት። በአጠቃላይ ግን የዘንድሮው ምርጫ ውጤት፤ ያውሮፓ አክራሪ ብሄረተኖችና ወግ አጥባቂዎች ጎልተው የወጡበት፤ አውሮፓም ከበርክታ አመታት ወዲህ ወደቀኝ ያደላበት ሆኖ ታያቷል። ይህም በተለይ በአየር ንብረት ለውጥ፤ የስደተኖች፤ የመከላከያና የዩክሬን አጀንዳዎች ላይ የህብረቱን አገሮች አንድነት ሊፈታተን እንደሚችል ነው ታዛቢዎች ከወዲሁ የሚናገሩት።


ገበያው ንጉሴ

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ