1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዋስትና የተፈቀደላቸው የኦነግ አባላት እንዳልተፈቱ ጠበቃቸው ተናገሩ

ረቡዕ፣ ጥር 12 2013

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አባላት የሆኑ ፖለቲከኞች ድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ከተገደለ በኋላ በተቀሰቀሰ ኹከት ተጠርጥረው ከታሠሩ በኋላ ፍርድ ቤት ዋስትና ቢፈቅድላቸውም እስከዛሬ አልተፈቱም። ጠበቃቸውን ቱሊ ባይሳ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ዋስትና ተፈቅዶላቸው ሳይፈቱ ከቀሩት መካከል ለሚ ቤኛ፣ ዳዊት አብደታ እና ኮሎኔል ገመቹ አያና ይገኙበታል።

https://p.dw.com/p/3oBE1
 Logo Oromo Liberation Front

ዋስትና የተፈቀደላቸው የኦነግ አባላት እንዳልተፈቱ ጠበቃቸው ተናገሩ

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አባላት የሆኑ ፖለቲከኞች ድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ከተገደለ በኋላ በተቀሰቀሰ ኹከት ተጠርጥረው ከታሠሩ በኋላ ፍርድ ቤት ዋስትና ቢፈቅድላቸውም እስከዛሬ አልተፈቱም። ከእነዚህ መካከል ለሚ ቤኛ፣ ዳዊት አብደታ እና ኮሎኔል ገመቹ አያና ይገኙበታል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አወል ሱልጣን ግን በዋስትና የተፈታ ሰው ተጠርጣሪ የዋስትና ጊዜውን ጠብቆ ወደ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ቀርቶ ትዕዛዝ ከተሰጠ ብቻ ነው። 

ስዩም ጌቱ 
ሸዋዬ ለገሠ