ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኖች መዳኛ ፍርድ ቤት በሩሲያ ላይ ክስ
ማክሰኞ፣ የካቲት 29 2014ነገ ሁለተኛ ሳምንቱን በሚይዘዉ ሩሲይ በዩክሬን ላይ በጀመረችዉ ወረራ ሰበብ አሁንም ብዙዎችን እየተገደሉ፣ እየተፈናቀሉና እየተሰደዱ ነው። ከሩስያ የጦር ጀቶች በሚወረወሩ ሮኬቶች በተለይ ሃርከፍ፤ ማርዮፖል እና ኦዴሳን የመሳሰሉ ከተሞች መሰረታዊ ልማቶች ወድመዋል እየወደሙም ነው። የተመድ በዚህ ሳምንት ይፋ ባደረገዉ መረጃ እስካሁን ከ400 በላይ ዩክሬናዉያን ሰላማዊ ዜጎች በጦርነቱ ሞተዋል። ከ1,5 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ሃገር ጥሎ ተሰዶአል። ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት በኋላ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ይህን ያህል ሰዉ ከአንድ አገር ሲሰደድ በዩክሬን የመጀመርያዉ ነዉ ተብሎአል።
አስራ ሶስተኛ ቀኑን የያዘው የሩሲይ ዩክሬን ጦርነት አሁንም ብዙዎችን እየገደለ፣ እያፈናቀለና እያሰደደ ነው። መሰረታዊ ልማቶች እየወደሙና ከተሞች እየፈረሱ ነው። እስካሁን ከሞቱትና ከከቆሰሉት በርክታ ዩክርናውያን በተጨማሪ ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለስደት ተዳርገዋል። ዓለም በተለይም የምዕርቡ ዓለም ጦርነቱን በማውገዝ ላይ ነው። ሩሲያ ጦርነቱን እንድታቆምና ከዩክሬን እንድትወጣ በመጠየቅ፤ በተለይ የአውሮጳ ኅብረተና የኔቶ አገሮች ከወታደራዊ ርምጃ በመለስ በሞስኮና መሪዎቿ ላይ ያልወሰዱት ርምጃ ያላስተላለፉት ውሳኔ የለም ማለት ይቻላል። ከስሜን አሜሪክና አውሮጳ ጋር ግንኑነት ያላቸውና የተሳሰሩ የፋይናንስ ተቋሞች፣ ኩባንያዎች፣ የንግድና የአቴክኖሎጂ ተቋማት፤ የልዩ ልዩ የስፖርት ድርጅቶችና ቡድኖች ጭምር በሩሲያ ላይ እጁን ያላነሳ የለም። ይሁን እንጂ ሁሉ ርምጃና የውሳኔ ጋጋታ ዩክሬንን ሊታደጋት አልቻለም።
የዩክሬን መሪዎች በሩሲያ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለመከላከል እሳክሁን ከተላለፉት የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ውሳኔዎች በተጨማሪ የዩክሬንን ሰማይ ከሩሲያ አውሮፕላኖች በመከላከል እየደረሰ ያለውን ጥቅት በተግባር እንዲከላከሉላቸው እየጠየቁ ነው። ሆኖም ግን የዚህ ጥያቄ አዎንትዊ ምላሽ ጦርነቱን ከዩክሬን አልፎ በአውሮጳ ደረጃ እንዳያሰፋውና ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ጉዳት እንዳይስከትል በመስጋት እስካሁን ምዕራባውያኑ ጆሮ አልሰጡም። የጦር መሳሪያና የቁሳቁስ ርድታ ግን በገፍ ወደ ዩክሬን እይተላከ እንደሆነ ነው የሚነገረው። ከዚህ አልፎ አንዳንድ የኔቶ አባል አገሮች የተዋጊ አውሮፓላኖች ጭምር ለዩክሬን እኒዲሰጡ ምክክር እይተደርገ እንደሆነም እየተገለጸ ነው። ዘሄግ ኒዘርልንድስ የሚገኘው ዓለማቅፉ የጦር ወንጀለኖች መዳኛ ፍርድ ቤትም በሩሲያ ላይ ክስ ለመመስረት ምርመራ መጀምሩን ባለፈው ሳምንት ዐስታውቋል። የፍርድ ቤቱ ዋና አቃቤ ሕግ ሚስተር ካሪም ክሃን ፕሬዝዳንት ፑቲንን ጨምሮ የሩሲያን የጦርና የሲቪል መሪዎችን በጦርና የሰባዊነት ወንጀሎች ለመክሰስ የሚያስችሉ መረጃዎች የተሰበሰቡ መሆኑን በመግለጽ ክስ ለመመስረት ዝግጁ መሆናቸውን ዐስታውቀዋል።
የሄጉ ዓለምአቀፍ የወንጀሎች መዳኛ ፍርድ ቤት 123 አባል ገሮች ያሉት ሲሆን የዘር ማጥፋት፣ የጦርና ሰባዊ ወንጀሎችን እንዲሁም አገር የመውረርን ወንጀሎችን የሚዳኝ ተቋም ነው። ፍርድ ቤቱ እ እ በ1998 ዓም በተፍረመውና የሮማ ሰነድ በሚባለው ድንጋጌ የተፈረመ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም 123 አገሮች የስነዱ ፈራሚ አባሎች ናቸው። ዓላማውም በየአገሮቻቸው ሊታዩ ያልቻሉ ወይም መንግስታቱ ሊዳኟቸው ያልፈለጉ የዘር ማጥፋት፣ የጦርና ሰባዊነት ወንጀሎችን የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን ለመዳኘትና ተጠያቂነትን ለማስፈን እንደሆነ ሲገልጽ ቆይቷል። አባል ያልሆኑ አገሮች የሮማውን የማቁቋሚያ ሰንድ ያልፈረሙ አገሮች ግን በፍርድ ቤቱ እንዲዳኙ አይገደዱም። ሩሲያና ዩክሬን የፍርድ ቤቱን ሰነድ ያልፈረሙ ሲሆን፤ አሜርካም እንደዚሁ ካልፈረሙት አገሮች ውስጥ ናት።
ፍርድ ቤቱ በተቋቋመለት አላማ መሰረት ስራውን በትክክል በመስራት በተለያዩ ግዚያት በተለያዩ በታዎች የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በመመርመር ተጠያዊቆችን በፍጥነት ለፍርድ በማቅረብ በኩል በርካታ የሚስነዘሩበት አስተያየቶችና ወቀሳዎች አሉ። እስክሁን ከአውሮፓ በቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ በተክሰተው የርስ በርስ ጦርነት ጥቂት ወንጀሎኞችን ከማቅረብ ውጭ ብዙ ትኩረቱ በአፍሪካ ላይ እንድነበረና በተለይ የምዕራብ አገሮች በተለያዩ አገሮች የፈጸሟቸውን ወንጀሎች አይቶ እንዳላየ ያልፋል በመባል ሲከሰስ ቆይቷል። በዚህም በተለይ ከአፍርካ አገሮች ተቃውሞ ሲሰማበት ቆይቷል። አሁን ሩሲያ በዩክሬን ላይ የክፈተችውን ጦርነት ተከትሎ የሩሲያ መሪዎችን ለፍርድ ለማቅርብ የጀመረው የምርመራና የክስ ሂደት ስኬት ከውዲሁ ባይታወቅም ብዙ ችግሮች እንደሚያጋጥሙት ግን ይግመታል።
በፍድር ቤቱ መተዳደሪያ ደንብ መስረት የፍርድቤቱ ዓቅቢ ሕግ በአንድ አገር ወይም ግለሰብ ላይ ክስ የሚመሰርተው በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክርቤት ሲመራ ወይም በአባል አገሮች ሲጠየቅ እንደሆነ ይታወቃል።
የአሁኑ የሩሲያ ክስም አርባ በሚሆኑ የፍርድ ቤቱ አባል አገሮች በመጠየቁ እንደሆነ ተገልጿልሏል። ብዙዎቹ ጥያቄውን ያቀረቡ አገሮች ጀርመንና ፈረንሳይን ጨምሮ የውሮፓ ገሮች እንደሆኑ ታዉቋል። ፍርድ ቤቱ ወንጀል ተፈሟል በሚባሉ ቦታዎች ላይ ክስ ለመመስረትም ሆነ ተጠያቂዎችን ለፍርድለማቅረብ አዝጋሚ ነው ይባል የነበረ ቢሆንም በሁኑ ወቅት ግን ፈጥኖ እንደተንቀሳቀሰ ነው የሚነገረው ። ቀድሞ የመንግስቱ ድርጅት ልዩ አቃቤ ህግ የነበሩት ሚስተር ፓያን እንደሚሉት ይህ የሆነው የአሁኑ ሁኒታ ልዩና አሳስቢ በመሆኑ ነው።ድምጽ በዩክሬን የተፈጸመውና እየተፈጸምያለው ወንጀል ያልተጠበቀና ትልቅ ሰባዊ ቀውስ የፈጠረ ነው። የፍርድ ቤቱ ሃላፊነትና ተግባር ክስ መመስረት ብቻ ሳይሆን የሚፈጸሙ ወንጀሎችንም መከላከል በመሆኑ እርምጃው ወንጀል ፈጻሚዎችን ወንጀላቸው በዓለም አቀፍ አደባባይ የተጋለጠ መሆኑ እንዲያውቁና ምናልባትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሊያግዝ ይችላል ሲሉ የመፍጠኑን አስፈላጊነትና ጠቃሚነትገልጸዋል።
ይሁን እንጂ ክሱም ሆነ በወንጀል መፈረጁ የሩሲያንና የፕሬስሻንት ፑቲንን እርምጃ ማቆም መቻሉን ብዙዎች ይጠራጠርሉ። ሚስተር ዋይኔ ጆርዳሽ የተባሉ የተባሉ ባለሞያም ይህን ጥርጣሬ በመጋራት ድምጽ ፑቲን የራሱ ህዝብ ተነስቶ አቁም ካላለው በስተቀር በሌላ ማንም ሀይል ማቆም መቻሉን እጠርጠራሉ በማለት የፍርድቤቱ ሂደት ጦርነቱን ለማስቆም ያለው ጉልበት ውስን ወይም ደካማ መሆኑን እሳቸውም እንደሚያምኑ ነው ያስረዱት። ያ፤ ሆኖ ግን አለማቀፉ ማህብረሰብ ሊያደርግ የሚገባውን ማድረግ እንዳለበተና የአለማቀፉ ፍርቤት የክስ ሂደትም ትክክለኛ ርምጃ እንደሆነ ነው ሚስተር ጆርዳሽ የሚናገሩት።
እንደሂውማን ሪይትስ ዋች ያሉ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችም ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት መቅረቡንና የክስ ሂደት መጀመሩን ተገቢና ወቅታዊ ብለውታል። በዓለማቀፍ ኅብረተሰብ ጉድዩ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንዲታይ መጠይቁ በራሱ ጦርነቱ የፈጠረውን አለምቀፍ ስጋትና የደረሰውን ሰብዊ ቀውስ ጥልቀት የሚያሳይ ነው በማለትም የፍርድ ቤቱ እንቅስቃሴ ለጦርነቱ መቆም አስተዋጾ ሊያደርግ ይችል ሲሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ ብዙዎች ክሱ አስገዳጅነት ኖሮትና በፕሬዝድንት ፑቲን ላይ ተፈጻሚነት ኖሮት ፍትህ ሲበየን አይታያቸውም። እንደው ፕሪዝዳንት ፑቲን አለማቀፉ ፍርድ ቤት ላይ ስቀርቡ ይታየወታል ወይ ተብለው የተጠይቁት የቀድሞው የመንግስቱ ድርጅት አቃቤ ሕግ ሚስተር ፓያም አክሃቫን መልሳቸው ማን ያውቃል የሚል ነው የሚመስለው ድምጽ ጠጥያቂ የሚሆነውን አሁ መገመት ይስቸግራል። አቃቤ ሕግ መረጅው ወደሚወደው ነው የሚሀደው ሆኖም ግን አንድ ጊዜ የክስ ማዛዣ ከወጣ በኋላ በእርግጥ የሮማውን ስነድ ያልፈረሙ አይገደዱም ግን ማዘዛ የተቆረጠበት ሰው አባል ወደሆኑት የአውሮፓ አገሮች አይገባም ። ክራሴ ልምድ የተነዘብኩት ዛሬ በስልጣን ላይ ያለ ነገም በበስልጣን አይቆይም በማልት ከስልጣን ከወረዱ ብኋላ በላመቀፉ ፍርድ ቤት ቀረበው የተዳኙትን የሴርቢያውን ሚስተር ሚሎሶቪች በምሳሌነት በመጥቀስ ስራው ግን ከወዲሁ መሰራት ይኖርበታል ብለዋል።
በበሌላ በኩል አሁን ትኩስ ጦርነት እይተካሄደ ባለበት ወቅት ከተፋልዎቹ ወገኖች ባንዱ ላይ ክስ መመስረቱ በጭር ጊዜ ተኩስ ለማቆምና ሰላም ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት እንደውም ሊያሰናክል ይችላል የሚሉ ተክራካርዎችም አሉ። የሕግ ባለሞያ ሄዲ ማቲውስ እንደሚሉት ሲፋለሙ በነበሩና ሰላም ባወረዱ ወገኖች መካከል ተጠያቂዎችን ለፍርድ ለማቅረብ መሞከርና እየትከሄደ ባለ ትኩስ ጦርነት ምሀል ከተፋላሚዎቹ ባንዱ ላይ ክስ መመስረት ይለያል። ዕንደውም እንደዚህ ያለው እርምጃ ችግሩን ሊያባብሰውና ውስብስብም ሊያደረገው ይችላላ በማለት ስጋታቸውን ይገልጻሉ።
እናም እነዚህ ወገኖች ጦርነቱን ለማስቆም መጀመሪያ ለጦርነቱ መቀስቀስ ምክኒያት በሆኑት አጀንድዎች ላይ በድርድር ፖቲካዊ መፍሄ መፍለግና ሰላም መፍጠር መቅደም ያለበት መሆኑን በማስታወስ የፍርድና የፍትሁ ሂደቱ በቀጣይ የሚመጣና ለዘላቂው ሰላምም ወሳኝ ሆኖ ሊሰራበት እንደሚገባ ያስገንዝባሉ።
ገበያው ንጉሤ
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ