ዛሬ ማታ ጀርመን ዴንማርክን በቀላሉ ያሸንፋል ሲሉ ብዙዎች ገምተዋል፤ እናንተስ?
ቅዳሜ፣ ሰኔ 22 2016ማስታወቂያ
የቦሩስያ ዶርትሙንድ የእግር ኳስ ቡድን ንብረት በሆነው «ሲግናል ኢዱና ፓርክ» ስታዲየም በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ዛሬ ማታ አራት ሰአት ላይ ጀርመን የዴንማርክ ቡድንን ይገጥማል ። በጉግል የተጠየቁ በርካቶች ከምድብ «ሀ» አንደኛ ሆኖ 16 ቡድኖች ወዳሉበት ጥሎ ማለፍ ውድድር ያለፈው የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ዴንማርክን አሸንፎ ወደ ሩብ ፍፃሜ ያልፋል ብለዋል ። ዴንማርክ ከምድብ «ሐ» እንግሊዝን ተከትሎ በሦስት ነጥብ ሁለተኛ ሆኖ ነው ያለፈው።
የአውሮጳ እግር ኳስ የምሽቱ ውድድርን በተመለከተ መጠይቅ ከተደረገላቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ጀርመን ያሸንፋል ሲሉ የገመቱት ከግማሽ በላይ ማለትም፦ 59 ከመቶ ናቸው ። ዴንማርክ ያሸንፋል ሲሉ የገመቱ ደግሞ 17 ከመቶ ብቻ ሆነዋል ። ጀርመን ዛሬ ማታ ካሸነፈ ምናልባትም በሩብ ፍጻሜው የሚጋጠመው ከስፔን ጋ ሊሆን ይችላል ። ብዙዎች ስፔን ጆርጂያን ነገ በቀላሉ ማሸነፉ አይቀርም ሲሉ ገምተዋል ።
እናንተስ ማን አሸንፎ ወደ ሩብ ፍፃሜው ያልፋል ትላላችሁ? ግምታችሁን በፌስቡክ ገጻችን አስተያየት መስጪያ እያሰፈራችሁ ተሳተፉ ። ስዊትዘርላንድ እና ጣሊያንም ዛሬ ይጋጠማሉ ።ከዶርትሙንድ ተጨማሪ የምስል፣ የቪዲዮ እና የድምፅ ዘገባዎች ይኖሩናል ። #DWSports
ማንተጋፍቶት ስለሺ