1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: «የአየር ንብረት ለውጥ የድምፅ መግለጫ መድረኬ ነው»

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 2 2017

የ 17 ዓመት ታዳጊዋ ኢየሩሳሌም ሰለሞን በትምህርቷ ታታሪ ከሚባሉትና ጥሩ ውጤት ካላቸው መካከል አንዷ ናት። ከትምህርቷ ጎን ለጎን በበጎ ፈቃድ ተግባራት ትሳተፋለች፤ በዓየር ንብረት ለውጥ ጥበቃ ዓለም አቀፍ ተቋም ጋር ትርጉም ያለው ሥራ ትሠራለች፤ ወደፊትም በዲፕሎማሲ የሥራ መስክ ሀገሯን የማገልገል እና መሪ የመሆን ፍላጎት አላት።

https://p.dw.com/p/4o069

ኢየሩሳሌም በትምህርት ቤቷ የተማሪዎች አምባሳደር ጭምር ነች። በአንድ በኩል ታታሪ መሆንና በትምህርት ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ መቻል፣ ከትምህርት ውጪ ደግሞ ሁለገብ ተሳትፎ ውስጥ ከእኩዮች ጋር መሳተፍ መቻልን ገና በታዳጊነት ዕድሜ ማስኬድ መቻል ብልህነትንም አርቆ አስተዋይነትንም ያሳይል። ይህ የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ኢየሩሳሌም ሰለሞን ልዩ ችሎታ ነው።
#ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘገባ፡ ሱመያ ሳሙኤል
ቪዲዮ፡ ሰለሞን ሙጬ