1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሳዑዲ ድንበር ጠባቂዎች ኢትዮጵያዉያንን ገደሉ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 17 2015

ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት እንደሚለዉ የሳዑዲ አረቢያ ወታደሮች ጥይታቸዉን በስደተኞቹ ላይ «እንደ ዝናብ አዉርደዉታል።»

https://p.dw.com/p/4VSEA
የሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን የገደሉበት ቦታ
የሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን የገደሉበት ቦታ ምስል Human Rights Watch

የሳዑዲ ወታደሮች «ጥይታቸዉን በስደተኞቹ ላይ እንደ ዝናብ አወረዱት»ሑዩማን ራትስ ዋች

                        

የሳዑዲ አረቢያ ጦር ኃይል ከየመን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመግባት የሞከሩ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን በጥይት ደብድቦ መግደሉን ሁዩማን ራይትስ ዋች አጋለጠ።ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት እንደሚለዉ የሳዑዲ አረቢያ ወታደሮች ጥይታቸዉን በስደተኞቹ ላይ «እንደ ዝናብ አዉርደዉታል።»

ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች-የመንና ሳዑዲ አረቢያ ድንበር
ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች-የመንና ሳዑዲ አረቢያ ድንበር ምስል Khaled Abdullah/REUTERS

የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም የሳዑዲ አረቢያ ወታደሮች በየመን በኩል አቋርጠዉ ሳዑዲ አረቢያ ለመግባት የሚሞክሩ ስደተኞችን በተለያየ ጊዜ መግደላቸዉን አረጋግጧል።የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ግን ወቀሳዉን አልተቀበለዉም።

የታጠቁ የሳውዲ አረቢያ ጠባቂ ወታደሮች፣በየመን በኩል አድርገው በእግራቸው በአሁኑ ሰዓት ውደ ግዛታቸው ለማለፍ በሚሞክሩት የኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ „…ጥይታቸው እንደ ዝናብ በእነሱ ላይ አርከፍክፈው በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት አጥፍተዋል።»

የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሰቆቃ በሳዑዲ እስር ቤቶች

ይህን የሚለው እዚህ ትላንት የወጣው ለሰበዓዊ መብት መከበር በዓለም ዙሪያ በአሁኑ ጊዜ የሚሟገተው «HRW የተባለው ድርጅት ነው፡፡ አውሮጳ የተበተነው ሰነድ ረዥም ነው፡፡ከ70 ገጾች በላይ ይዞአል፡፡

በፊልምና በድምጽ ፣በበርካታ ማሽረጃችም ተደግፎ ፣ለሰበኣዊ መብት መከበር በዓለም ዙሪያ የሚሟገተው HRW የሚባለው ድርጅት „ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ስደተኞን፣ሕጻናት ልጆችን እና እናቶችን ጭምር  በጅምላ ድንበሩ ላይ በጥይትና በፈንጂ ቦንብ ገድሎአቸዋል“ ብሎ የሳውዲን መንግሥት ከሶአል፡፡

በጅቡቲ አድርገዉ የመን፣ከየመን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመግባት የሚጓዙ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች
በጅቡቲ አድርገዉ የመን፣ከየመን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመግባት የሚጓዙ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችምስል Nariman El-Mofty/AP Photo/picture alliance

„መሠረት የሌለው የፈጠራ ክስ ነው „ ብሎም የሳውዲ መንግሥት አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው „…ክሱን በበኩሉ ውድቅ አድርጎት ለማለፍ ሞክሮአል፡፡“

„በእኛ እምነት ሚሰተር ሳም ዱበርሊ- የድርጅቱ ተጠሪ በጀርመን አገር ለጣቢያችን ለ ዲ ደብልዩ እንደ አሉት - „በእኛ እምነት፣ በድምበሩ ላይ በአለፉት ጊዜያት የሰበሰብናቸው መረጃዎች፣እንዲሁም የዓይን ምስክሮች እንደሚያረጋግጡት፣ከባድ መሣሪያ የታጠቁት የሳውዲ ወታደሮች ለስደተኞቹ ሕይወት መጥፋትና እነሱ ተጠያቂዎች እንደሆኑ በቂ ማሥረጃዎች በእጃችን ላይ አሉን „ ብለዋል፡፡

ሳውዲ ውስጥ በሚኖሩትና የቤት ሠራተኞ እና በሌሎቹም የኢትዮጵያ ዜጎች ላይ ላይ እዚያ የሚፈጸመው በደልና ጥቃት ግዲያም ጭምር - ተመልካቾች እዚህ እንደሚሉት - አዲስ ነገር እንደአልሆነ ይታወቃል፡፡

ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በየመን
ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በየመን ምስል Mohammed Mohammed/dpa/picture alliance

„ልዩ የሚያደርገው ሚሰተር ሳም ዱበርሊ -ተጠሪው- እሳቸው ለጣቢያችን አያይዘው እንደ አሉት „አንድ ነገር ነው፡፡“

„ እኛ በየመንና በሳውዲ ድንበር ላይ የሚካሄዱትን ማንኛውንም ነገሮች፣እስከ ግድያ ድረስ ለአለፉት ስምንትና ዘጠኝ አመታት በቁራኛ ዓይን ስንከታተለውና ስንዘግበው ቆይተናል፡፡ ይህኛው ህን በመጠኑና በስፋቱ እንዲሁም በሟቾቹ ቁጥርም፣በአገዳደሉም ጭቃኔ፣ከአለፉት አመታት እጅግ የከፋና የተለየ ነው“ ብለዋል፡፡

ሳውዲንና እና የመንን የሚያዋሰወነው ድንበር ሰው የማይደርስበት ድንጋያማ በረሃ በመሆኑ፣ለምን የድንበር ጠባቂዎቹ እንደዚህ ዓይነቱን ግድያና ግፍ እዚያ በስደተኞቹ ላይ እንደፈጸሙ መልስ መስጠት ያለበት ክፍል ቢኖር „ ተጠሪው እዚህ እንዳሉት“ የሳውዲ መንግሥት ብቻ ነው፡፡“

 

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ