የሶማሊያ መንግስት ጥያቄ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዉሳኔ
ቅዳሜ፣ ነሐሴ 18 2016የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮርፖሬት ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ ወይዘሮ ሐና አጥናፉ በተነሳው ጥያቄ ላይ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋር ንግግር ከተደረገ በኋላ ስምምነት ላይ መደረሱንና በረራውም እንዲቀጥል መደረጉን ዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 18 ለዶቼ ቬለ አረጋግጠዋል።
የሶማሊያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ጉዳዩን ከሀገሪቱ ሉዓላዊነት ጋር በማገናኘት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀረበለትን ጥያቄ ካላስተካከለ ወደ ሶማሊያ የሚያደርገውን በረራ ሊያግድ እንደሚችል አሳስቦ ነበር።
ሶማሊያ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ያነሳችው ቅሬታ ስለመፈታቱ
ሶማሊያ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ያነሳችው ቅሬታ በአየር መንገዱ ድረ -ገጽ እና የቲኬት መቁረጫ መተግበሪያ ላይ ስለመስተካከሉ ያረጋገጥን ሲሆን፣ ሀርጌሳ በሚል በምርጫ ዝርዝር ላይ ተጠቅሶ የነበረው የበረራ ማሳወቂያ አሁን ከፊት ሀርጌሳን አስቀድሞ ከስር ሶማሊያ የሚለውን ስም አካትቶ ማስቀመጡን ተመልክተናል። ይህ ማስተካከያ ስለመደረጉ ማረጋገጣቸውን ከሶማሊያ የሚወጡ ዘገባዎችም ያሳያሉ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድን በርካታ በረራዎች ያስረዘው የትናንቱ የአየር ሁኔታ
የሶማሊያ መንግሥት ከሦስት ቀናት በፊት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ በፃፈውና በማሕበራዊ መገናኛ ዐውታሮች በስፋት በተሰራጨው ደብዳቤ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሀርጌሳ፣ ሶማሊላንድ በሚል ያስቀመጠው የበረራ ቦታ መግለጫ የሶማሊያን ሉዐላዊነት የሚጥስ ነው በሚል ማስተካከያ እንዲደረግ፣ ይህም እስከ ትናንት አርብ ካልተስተካከለ አየር መንገዱ ወደ ሶማሊያ የሚያደርጋቸውን በረራዎች ለማገድ እንደሚገደድ ጠቅሶ ነበር።
ይህንኑ በተመለከተ ዛሬ ነሐሴ 18 ዶቼ ቬለ ጥያቄ ያቀረበላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮርፖሬት ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ ወይዘሮ ሐና አጥናፉ ችግሩ ተፈትቷል፣ በረራዎችም ይቀጥላሉ ብለዋል።
"ትናንትና ስምምነት ላይ ደርሰናል። ከሶማሊያ ሲቪል አቪየሽን ሰዎች ጋር ተነጋግረናል። ስምምነት ላይ ደርሰናል። በረራችን አይቆምም። የሚቀጥል ነው የሚሆነው።
በባለስልጣናት የቃላት ምልልስ የቀጠለው የኢትዮ ሶማሊያ ዲፕሎማሲ ውጥረት
የሻከረው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ግንኙነት
ኢትዮጵያ ሶማሊያ የሉዓላዊ ግዛቴ አንድ አካል ናት የምትላት ነገር ግን ራሷን ራስ ገዝ አድርጋ ከምትንቀሳቀሰው ሶማሊላንድ ጋር የባሕር በር ተጠቃሚነትን የሚያስገኝ የመግባቢያ ስምምነት መፈረሟን ተከትሎ ክፉኛ የሻከረው የኢትዮ ሶማሊያ ግንኙነት ወደ ከፋ ሁኔታ እንዳያመራ መፍትሔው ምንድን ነው? ስንል ሰሞኑን የጠየቅናቸው በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህሩ ዶክተር ሙዐዝ ግደይ ይህንን ብለው ነበር።
አየር መንገዱ እስከ 2030 ዓ/ም የሚረከባቸው 125 አዳዲስ አውሮፕላኖች ሊገዛ ነው
"የኢትዮጵያ ውሳኔ ሌሎች ተመሳሳይ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን እና የመገንጠል ጥይልቄ ያላቸው ግዛቶችን መጥፎ ምሳሌ ይሆናል ስለሚባል ተቃውሞ ሊቀሰቅስ የሚችል ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያ በዚህ መልኩ እቀጥላለሁ ካለች ወደ ወታደራዊ ፍጥጫ ሊሄድ ይችላል ወይም ደግሞ በሰጥቶ መቀብል የሚመራ ከሆነ ያለው አማራጭ ሌሎች አማራጮችን መፈለግ ነው።"
ከዚህ በፊት ወደ ሀርጌሳ ሲጓዝ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ፈቃድ እንደሌለው ተገልጾ በሶማሊያ መንግሥት ትዕዛዝ እንዳይገባ ተደርጓል። በሌላ በኩል ከስድስት ወራት በፊት በሶማሊያ የአየር ክልል ውስጥ ሲበር የነበረ ሌላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ከሌላ አቅጣጫ ይበር ከነበረ የቃጣር አውሮፕላን ጋር በተመሳሳይ ከፍታ ላይ ሲበር መገኘቱ ውዝግብ ፈጥሮ አልፏል።
የኤርትራ መንግሥት የበረራ አገልግሎት እግድና ኢትዮጵያ አየር መንገድ ምላሽ
ኢትዮጵያ እና ሶሜሊያ በቱርክ አሸማጋይነት አንካራ ውስጥ ሁለት ጊዜ ወቅታዊ ልዩነታቸውን ለመፍታት ቀጥተኛ ያልሆነ (Shuttle Diplomacy) ንግግር ቢያደርጉም ዘላቂ መፍትሔ ያለው ውጤት ማምጣት አልቻሉም። በዚህም ምክንያት ለሦስተኛ ዙር ንግግር ለመስከረም 7 ቀጠሮ መያዛቸው ይታወሳል።
ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ