የሶማሌ ዑጋዛዊ ምክር ቤት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ተቃወመ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 21 2013ማስታወቂያ
የሶማሌ ዑጋዛዊ ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ በሶማሌ እና አፋር ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በሚገኙ ስምንት ቀበሌዎች ያሳለፈውን ውሳኔ በሚመለከት የክልሉ መስተዳድር ላቀረበው ጥያቄ ቦርዱ የሰጠውን ምላሽ ተቃወመ፡፡ ውሳኔውን “ግጭት ቀስቃሽ” ሲል አውግዞታል ፡፡
የሶማሌ ዑጋዛዊ ምክር ቤት ተጠሪ አቶ መሀመድ ሙሴ ጌሪ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት መግለጫ በቅርቡ ምርጫ ቦርድ ያሳለፈውን ውሳኔ እንደሚቃወሙ ፣ በጉዳዩ ላይ የክልሉ መንግስት ለቦርዱ ያቀረበውን ጥያቄ እንደሚደገፉ ገልጠው “ግጭት ቀስቃሽ” ያሉትን የቦርዱ ውሳኔ ቦርዱ እንዲመረምር ጠይቀዋል፡፡
ቦርዱ በስምንቱ የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ነዋሪዎች በአቅራቢቸው ባለ ምርጫ ጣቢያ እንዲመርጡ ይደረጋል የሚለውም ትክክል አለመሆኑን አቶ መሀመድ ተናግረዋል፡፡
የሲቲ ዞን ነዋሪው አቶ አደም ፈንታሌ በበኩላቸው “በብዙ ችግር ውስጥ ባለችው ሀገር ላይ ሌላ ችግር መሆን አንፈልግም በሰላማዊ መንገድ ላቀረብነው ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ ይሰጠን” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
የኢትዮጵ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሶማሌ እና አፋር ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በሚገኙ ስምንት ቀበሌዎች ምርጫ ዙርያ ያሳለፈውን ውሳኔ በሚመለከት ከሶማሌ ክልላዊ መስተዳድር ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡
መሳይ ተክሉ
ሸዋዬ ለገሠ