የሶሪያ ስደተኞችና ቱርክ
ረቡዕ፣ የካቲት 2 2008ማስታወቂያ
በሶሪያዋ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ አሌፖ በሚካሄደው የአየር ድብደባ ምክንያት በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሶሪያውያን ወደ ቱርክ መሰደዳቸው ቀጥሏል ። ይሁንና በርካታ የሶሪያ ስደተኞችን የምታስተናግደው ቱርክ ድንበርዋን መዝጋትዋ ስደተኞችን ለከፋ ችግር አጋልጧል ። የተመድ ቱርክ ድንበሯን በመክፈት በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩትን እነዚህን ስደተኞች እንድታስገባ ጥሬ አቅርቧል ። ሩስያም በአሌፖ የምታካሂደውን የአየር ጥቃት እንድታቆም ጠይቋል ።ቱርክ ግን ከአሁኑ በኋላ የሚመጡ አዳዲስ ስደተኞችን የምታስገባው አስፈላጊ ከሆነ ብቻ መሆኑን አስታውቃለች ።በአሁኑ ጊዜ በርካታ ሶሪያውያን ወደ ቱርክ መግባት ተከልክለው ኦንኩፒናር በተባለው የድንበር ከተማ ውስጥ ይገኛሉ ።የእርዳታ ድርጅቶች እንደሚሉት በገላጣ ሜዳና በተጨናነቁ ድንኳኖች ውስጥ ያሉት እነዚህ ስደተኞች ለጤና ችግሮች ተጋልጠዋል ። ስለ ቱርክ እርምጃ የብራሰልሱን ወኪላችንን ገበያው ንጉሴን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ