1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀድሞ የሶማሌ ክልል ባለሥልጣናት ታሰሩ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 13 2013

የክልሉ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ተጠርጣሪዎች ቀደም ሲል በክልል ደረጃ  በሥልጣን ላይ የነበሩ እንደሆኑ መረጃውን ለዶቼ ቬለ ያረጋገጡት የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3zBTs
Somali Regional Police Logo
ምስል Mesay Tekelu/DW

«ሁከት እና ብጥብጥ እንዲፈጠር ሲሰሩ ነበር ተብሏል»

የሶማሌ ክልል እና አጎራባች አካባቢዎች ሁከት እና ብጥብጥ እንዲፈጠር ሲሰሩ ነበር የተባሉ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ። የክልሉ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ተጠርጣሪዎች ቀደም ሲል በክልል ደረጃ  በሥልጣን ላይ የነበሩ እንደሆኑ መረጃውን ለዶቼ ቬለ ያረጋገጡት የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በክልሉ የፀጥታ ስጋት እንደሌለ በማመልከትም የፀጥታ ኃይሉ ከሚወስደው ርምጃ በተጨማሪ ኅብረተሰቡ ከዚህ ቀደም የደረሱ አስከፊ ችግሮች እንዳይደገሙ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር እየሠራ ነውም ብለዋል።

መሳይ ተክሉ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ