የቤልጅግ የተገን ጠያቂዎች ቢሮ ውሳኔ
ዓርብ፣ ነሐሴ 11 2010ማስታወቂያ
ብራስልስ ደቡብ ቢሯቸው ፊት ለፊት የሚገኘው ማክሲሚላን መናፈሻ "የህገ ወጥ ፍልሰተኞች" መናኸሪያ እየሆነ መምጣቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ይህንን እርምጃ ለመውሰድ እንደተገደዱ ሚኒስትሩ ቲዮ ፍራንከን ተናግረዋል። ወደ እንግሊዝ ለመግባት ከተለያዩ ቦታዎች የሚሰባሰቡት እነዚሁ ፍልሰተኞች መጨረሻቸው ምን እንደሆነ ባይታወቅም እኚሁ ሚኒስትር ግን ወደ "ሀገራቸው በግድም ቢሆን እንመልሳቸዋለን" ሲሉ ተደምጠዋል። በመጪው ጥቅምት 2018 ሀገር አቀፍ ምርጫ የምታካሒደው ቤልጅግ የፖለቲካ ፓርቲዎቿ የተገን ፈላጊዎችን ጉዳይ እንደ አንድ የምርጫ ቅስቀሳ መሳሪያም ይጠቀሙበታል። ውሎ አዳራቸው በእዚህ መናፈሻ ስፍራ ካደረጉ መካከል የኢትዮጵያውያኑን ሁኔታ ከዚህ ቀደም በሳምንታዊ መሰናዶ ያስደመጠን ዳግማዊ ሲሳይ ከብራስልስ ይህ ውሳኔ ይፋ ከሆነ በኋላ ያለውን እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።
ዳግማዊ ሲሳይ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ