1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤቶች ፈረሳና እርምጃዉ ያስከተለዉ ጣጣ

እሑድ፣ ሐምሌ 10 2008

በአዲስ አበባ ከተማ በሕገ ወጥ የተገነቡ ናቸዉ የተባሉ ቤቶች ፈረሳ እየተካሄደ ነዉ። በግንቦት ወር በአዲስ አበባ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ገርጂ አካባቢ ወረገኑ የሚባል ቦታ ላይ “በሕገ ወጥ የመሬት ወረራ ተገንብተዋል” የተባሉ ከ2 ሺሕ በላይ ቤቶች መፍረስ ሲጀመር፣

https://p.dw.com/p/1JQJN
Ärger über angeblichen Abriss der illegal gebauten Häuser in Addis Äthiopien
ምስል DW/G.Tedla

የቤቶች ፈረሳና እርምጃዉ ያስከተለዉ ጣጣ


በአፍራሽ ግብረ-ኃይሉ እና “ቤታችንን አናስፈርስም” ባሉ ነዋሪዎች መካከል በተነሳ ውዝግብ ቢያንስ 3 ሰዎች እንደሞቱ እና ከ50 በላይ እንደተጎዱ ተዘግቧል። ይህ በሆነ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በሰኔ ወር አጋማሽ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ሰኔ 22 በተመሳሳይ “ከሕገ ወጥ ቤት መፍረስ ጋር በተያያዘ” በአካባቢው ነዋሪዎችና በፖሊስ መካከል በተነሳ ግጭት የሰው ሕይወት ጠፍቶአል። በዚህ አካባቢ ይፈርሳሉ የተባሉት እስከ 20 ሺሕ ድረስ የሚገመቱ ቤቶች ናቸው። መንግሥት ቤቶቹን ለማፍረስ “ሕገ ወጥ” የሚለውን ቃል ቢጠቅስም ቤታቸው የፈረሰባቸው ነዋሪዎች ግን ከ6 እና 7 ዓመታት በፊት ቤቶቹን ሲሠሩ “ሕገ ወጥ ነው” ያላቸው የመንግሥት አካል እንደሌለ ይናገራሉ። ሕገ-ወጥ የተባሉት ቤቶች መፍረሳቸዉ ባያከራክርም፤ ቤቶቹ የፈረሱበት ወቅትና እንዲፈርስ የተደረገበት መንገድ አሁንም ማከራከሩ ቀጥሎአል። ሕገ-ወጥ የሚባሉ ቤቶች ፈረሳና እርምጃዉ ያስከተለዉ ጣጣ የእንወያይ ርእሳችን ነዉ። ሙሉ ዉይይቱን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።


አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ