1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብልጽግና ፓርቲ ውጤታማ ባልሆኑ አመራሮች ላይ እየወሰደ ያለው ርምጃ

ረቡዕ፣ መጋቢት 7 2014

የብልጽግና ፓርቲ ሰሞነኛ ውሳኔዎች እና አንድምታ ባለፈው ሰኔ በኢትዮጵያ በተደረገው ብሔራዊ ምርጫ አሸንፎ ስልጣኑን የያዘው ብልጽግና ፓርቲ ሰሞኑን ያደረገውን የመጀመሪያው ጠቅላላ ሀጉባኤ ተከትሎ የተለያዩ ውሳኔዎች አስተላልፏል ፡፡ ፓርቲው ትናንት እንዳስታወቀው የአመራር ክፍተትን አሳይተዋል የተባሉ 10 ሺህ ገደማ አመራሮቹ ላይ እርምጃ ወስዷል።

https://p.dw.com/p/48a0Y
Äthiopien Addis Abeba | Sitz der Prosperity Party
ምስል Seyoum Getu/DW

የብልጽግና ፓርቲ በሺ በሚቆጠሩ የስራ ኃላፊዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ

የብልጽግና ፓርቲ ሰሞነኛ ውሳኔዎች እና አንድምታ ባለፈው ሰኔ በኢትዮጵያ በተደረገው ብሔራዊ ምርጫ አሸንፎ ስልጣኑን የያዘው ብልጽግና ፓርቲ ሰሞኑን ያደረገውን የመጀመሪያው ጠቅላላ ሀጉባኤ ተከትሎ የተለያዩ ውሳኔዎች አስተላልፏል ፡፡ ፓርቲው ትናንት እንዳስታወቀው  የአመራር ክፍተትን አሳይተዋል የተባሉ 10 ሺህ ገደማ አመራሮቹ ላይ እርምጃ ወስዷል።  ከእነዚህ ውስጥም  ከ2 ሺህ በላይ የሚሆኑት ከኃላፊነታቸው ሙሉ በሙሉ የተወገዱ መሆናቸውን አሳውቋል፡፡ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ ተንታኝ ግን ውሳኔው በለጠ ለህዝቡ ግልጽነት የሚያስፈልገው ነው ብለዋል፡፡

 ፓርቲው ከመጋቢት 02 እስከ መጋቢት 04 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሶስት ተከታታይ ቀናት ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ የፓርቲው አመራሮች ሹም ሽሮችን ይፋ በማድረግ የትኩረት አቅጣጫዎችን ቢያስቀምጥም መንግስታዊ ስልጣን ላይ ለውጦች ካሉ ገና ይፋ አልሆኑም፡፡ ዶ/ር ደመላሽ መንግስቱ በጂማ ዩኒቨርሲቲ የኢንተርካልቸራል ኮሚዩኒኬሽን ተመራማሪ እና የኢትዮጵያን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉ ናቸው፡፡ እሳቸው ሃሳብ አስተያየታቸውን የሰጡንም ከፓርቲው አጠቃላይ የጉባኤው አቅጣጫ በመነሳት ነው፡፡

ፓርቲው ጉባኤውን ከመቀመጡን አስቀድሞ ህብረተሰቡ አሁን ላይ በሰፊው ለከፍተኛ ሰቀቀን ለተዳረገበት የሰላምና ፀጥታ ብሎም ለኑሮ ውድነት ፓርቲው እንደ ገዢ ፓርቲ የሚስቀምጠውን አቅጣጫም በጉጉት ነበር የሚጠብቀው፡፡ እንደ ዶ/ር ደመላሽ ማብራሪያ ግን በነዚህ ጉዳዮች በተለይም ሰላምና ፀጥታ በመላው አገሪቱ የሚሰፍንበት መንገድ ላይ የፓርቲው ጉባኤ ህዝብን ወርዶ ለማወያት ከመዘጋጀት ሌላ ግልጽ አቅጣጫ ያስቀመጠ አይመስልም ባይ ናቸው፡፡

 ፓርቲው በቅድመ ጉባኤ ግምገማው ላይ 2 ሺህ 574 አመራሮች ከሃላፊነት እንዲነሱ መደረጉን እና በ10 ሺህ 658 አመራሮች ላይ የተለያየ ደረጃ ያለው እርምጃ መውሰዱንም ትናንት ይፋ አድርጓል። የሙያ ስነ-ምግባር፣ የአገልግሎት ስብዕና እና የስራ ውጤታማነት የመገምገሚያ መስፈርቶቹ እንደነበሩም ተመላክቷል፡፡ ከዚህ ጋር አያይዘን እርምጃ ተወስዶባቸዋል የተባሉ አመራሩች የተጠያቂነት ደረጃ እና ለህዝብ ይፋ የሚሆንበት አግባብ ላይ የፓርቲውን ባለስልጣናት ተጨማሪ ማብራሪያ ለመጠየቅ ተደጋጋሚ ጥያቄ ብናቀርብም ለጊዜው ምላሽ አላገኘንም፡፡ ጥያቄውን ያቀረብንላቸው ዶ/ር ደመላሽ ግን፡

 የፖለቲካ ፓርቲ እና የመንግስት አመራሮች ለሚዲያ ቅርብ በመሆን ትችትና ምክሮችን ለመቀበልም ዝግጁ መሆን እንዳለባቸውም ምክረ ሀሳብ ቀርቧል፡፡

ሥዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ