1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመድ የልማት ፕሮግራም እና ጀርመን ለሰሜን ኢትዮጵያ የ10 ሚሊዮን ዮሮ ድጋፍ አደረጉ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 1 2016

በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን ለመርዳት የተባበሩት መንግታት ድርጅት እና የጀርመን መንግስት የ 10 ሚልዮን ዮሮ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ:: በሁለቱ ወገኖች የሚቀርበው የገንዘብ ድጋፍ በሰሜን ኢትዮጵ ይደረጋል የተባለውን የሰላም ስምምነት ለማፋጠን ያግዛል ተብሏል።

https://p.dw.com/p/4XTIo
Äthiopien Abkommen deutsche Regierung und UNDP | Friedensprojekt in Nordäthiopien
ምስል Hanna Demissie/DW

የተባበሩት መንግስታት እና የጀርመን የጋራ የገንዘብ ድጋፍ ለሰሜን ኢትዮጵያ

በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን ለመርዳት የተባበሩት መንግታት ድርጅት እና የጀርመን መንግስት የ 10 ሚልዮን ዮሮ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ::  በሁለቱ ወገኖች የሚቀርበው የገንዘብ ድጋፍ   በሰሜን ኢትዮጵ ይደረጋል የተባለውን የሰላም ስምምነት ለማፋጠን ያግዛል ተብሏል። 

ዛሬ ከቀትር በሁዋላ በኢትዮጵያ የጀርመን ኢምባሲ  ቅጥር ግቤ ውስጥ በኢትዮጵያ የጀርመን  አባሳደር ስቲፈን አሁሩ   መቀመጫቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉት የመንግስታቱ ድርጅት የልማት ፕሮግራም UNDP  ተወካይ ቱርሀን ሳላህ መካከል ነው ስምምነቱ የተፈረመው ። 

የጀርመን አምባሳደር  ስቲፈን አሁሩ በኢትዮጵያ ከመንግስታቱ ድርጅት ተወካይ ቱርሀን ሳላህ ጋር ፊርማቸውን ሲለዋወጡ
በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን ለመርዳት የተባበሩት መንግታት ድርጅት እና የጀርመን መንግስት የ 10 ሚልዮን ዮሮ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ::  በሁለቱ ወገኖች የሚቀርበው የገንዘብ ድጋፍ   በሰሜን ኢትዮጵ ይደረጋል የተባለውን የሰላም ስምምነት ለማፋጠን ያግዛል ተብሏል። ምስል Hanna Demissie/DW

አምና  በዚህ ወር መገባደጃ ላይ ጥቅምት 24 ቀን 2015 የፌደራል መንግስት እና የትግራይ ሀይሎች በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት  የሰላም ስምምነት መፈራረማቸውን ይታወሳል።  የጀርመን ርዳታ ለኢትዮጵያ

ዛሬ ከጀርመን መንግስት ጋር  ያደረግነው  ስምምነት  ይህንን  ሰላም እውን ለማድረግ የሚሰራውን ስራ ያፋጥነዋል  ሲሉ መቀመጫቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉት የ UNDP  ተወካይ ቱርሀን ሳላህ  ተናግረዋል። አያይዘውም  «ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው ሰላም ከሌለ እድገት የለም እድገት ከሌለ ደግሞ ሰላም የለም  ሰለዚህ ሁለቱም የማይነጣጠል ነው ሲሉ ተናግረዋል»  

«በኢትዮጵያ የጀርመን አንባሳደር አንባሳደር ስቲፍን አሁር   በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላም እና እድገትን ለማምጣት ለሚሰራው ስራ የጀርመን መንግስት  ያደረገውን የመጀመሪያው ይሆናል ብዬ ተስፋ የማደርገውን ስምምነት ለመፈራረም በመብቃቴ በጣም ደስተኛ ነኝ»  ብለው አያይዘው  በጦርነት ተጠያቂ የሆኑት አካላት ለፍርድ እስካልቀረቡ  ድረስ ዘላቂ ሰላም ማግኘት አይቻሉም » ሲሉ ተናግረዋል  ።

የጀርመን አምባሳደር  ስቲፈን አሁሩ በኢትዮጵያ ከመንግስታቱ ድርጅት ተወካይ ቱርሀን ሳላህ ጋር ፊርማቸውን ሲለዋወጡ
ከጀርመን መንግስት ጋር  ያደረግነው  ስምምነት  ይህንን  ሰላም እውን ለማድረግ የሚሰራውን ስራ ያፋጥነዋል  ሲሉ መቀመጫቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉት የ UNDP  ተወካይ ቱርሀን ሳላህ  ተናግረዋል።ምስል Hanna Demissie/DW

 በሰምምነቱ ወቅት ከጀርመን መንግስት የተለገሰው ገንዘብ በሰሜን ኢትዮጵያ በጦርነት ለተጎዱ ክልሎች ማለትም ለአፋር ፣አማራ እና ትግራይ ክልሎች እንደሚውል ተገልጿል ። ለተጠቀሱት ክልሎች በተናጥል የተመደበው ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ እና በምን ተግባር ላይ እንደሚውል ላቀረብኩት ጥያቄ መልስ ከመስጠት ተቆጥበዋል ። WFP ጀርመን ለኢትዮጵያ ድንገተኛ አደጋ 8.5 ሚሊዮን ይሮ መለገስዋን አወደሰ

 በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ኃይሎች ሁለት ዓመት ገደማ በተካሄደው ጦርነት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸውን ማጣታቸውን እና  የ29  ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የኢኮኖሚ ውድመት መድረሱ ይታውሳል ።  

ሃና ደምሴ

ታምራት ዲንሳ 

እሸቴ በቀለ