1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተደደር እና የፖለቲካ ተንታኝ ምን አሉ?

ማክሰኞ፣ ሰኔ 22 2013

መንግስት በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጠው ከትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር አርሶ አደሩ በክረምት ወቅት ማረስ እንዲችል ፣ ለችግረኞች በተሻለ ሁኔታ እርዳታ ማቅረብ እንዲቻልና በረሃ ካለው ኃይል መካከል ከመንግስት ጋር ተነጋግሮ ወደ ሰላም መንገድ ለመምጣት የሚፈልግ አለ የሚሉና ሌሎች ምክንያቶች ከቀረቡለት በኋላ ነው።

https://p.dw.com/p/3vmL9
Äthiopien I Konfliktregion Tigray
ምስል Ethiopian News Agency/AP/picture alliance

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እና የፖለቲካ ተንታኝ ስለተኩስ አቁሙ ምን አሉ

የፌዴራል መንግሥት ከትናንት ጀምሮ በትግራይ ክልል የተናጠል የተኩስ አቁም ማወጁን ይፋ አድርጓል። መንግስት በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጠው ከትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር አርሶ አደሩ በክረምት ወቅት ማረስ እንዲችል ፣ ለችግረኞች በተሻለ ሁኔታ እርዳታ ማቅረብ እንዲቻልና በረሃ ካለው ኃይል መካከል ከመንግስት ጋር ተነጋግሮ ወደ ሰላም መንገድ ለመምጣት የሚፈልግ አለ የሚሉና ሌሎች ምክንያቶች ከቀረቡለት በኋላ ነው።

በዚህ ጉዳይ ላይ መንግሥት የሰጠው ተጨማሪ ማብራሪያ የለም። ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቀጣይ ምን ሊደረግ ይችላል የሚለውን ለማወቅ ዶይቼ ቬለ ያደረገው ጥረት አልተሳካም።
አንድ የፖለቲካ ሳይንስ እና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህር እንዳሉት ውሳኔው አንድም ከአለም አቀፍ ጫና በሌላ በኩል መንግስት ትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኘውን የመከላከያ ኃይል ለመጠበቅ በሚል የወሰደው ስልታዊ እርምጃ ሊሆን ይችላል። በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድም ተቀባይነት ያለው እርምጃ የመሆን እድል እንደሚኖረውም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሐመድ