1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካ ቻይና እና ሩሲያ የአፍሪቃ ቀንድ የዲፕሎማሲ ጥረት አንድምታ

ሰኞ፣ ጥር 2 2014

አሜሪካና ምዕራባውያን ሸሪኮቿ በአንድ በኩል ቻይና እና ሩሲያ በሌላ ወገን ለአፍሪቃ አህጉር በተለይም በምሥራቅ አፍሪቃ ሃገራት በኢትዮጵያ በሱዳንና በሶማሊያ ለዓመታት ያንዣበበውን ፖለቲካዊና ወታደራዊ ቀውስ በሰላምና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት የየራሳቸውን የቀጣናው ልዩ ልዑክ እስከመሰየም ደርሰዋል።

https://p.dw.com/p/45MAd
Bundesmarine in Wilhelmshaven
ምስል AP

የአሜሪካ ቻይና እና ሩሲያ የአፍሪቃ ቀንድ የዲፕሎማሲ ጥረት አንድምታ

 እንደ ጎርጎርዮሳዊው የዘመን አቆጣጠር በ 2019 ዓ.ም ከፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ከሥልጣን መወገድ በኋላ ሦስቱ የሱዳን ወዳጆች አሜሪካ ኖርዌይና ብሪታንያ ከአውሮጳ ሃገራት ጋር በጥምረት በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ሽግግርንና ሰላምን ለማስፈን ይረዳል ያሉትን የሦስትዮሽ የጋራ መግለጫ ሲሰጡ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንም ኢትዮጵያ እና ሱዳንን ጨምሮ በአፍሪቃ ቀንድ ፖለቲካዊ ቀውሱን ለመፍታት ለአካባቢው ልዩ ልዑክ መሰየማቸው አይዘነጋም። የአፍሪቃ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት በበኩላቸው በኢትዮጵያ ያለውን ወታደራዊ ግጭት ለመፍታት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆን የሕብረቱ ከፍተኛ ልዑክ አድርገው ሲሰይሙ ከቀናት በፊት ኤርትራና ኬንያን በይፋ የጎበኙት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዩም ቤጂንግ በምሥራቅ አፍሪቃ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን ልዩ ልዑክ በቅርቡ እንደምትልክ ይፋ አድርገዋል። ይህ በተለይም ኃያላን ሃገራቱ ልዩ ልዑክ ጭምር በመሰየም የጀመሩት የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ በእውነት ለሃገራቱ ሰላምና እድገት ያለመ ነው ወይስ ሁለተኛው አፍሪቃን በእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ የመቀራመት ስልት ይሆን? ከዚህ እንቅስቃሴ ተጠቃሚውስ ማነው?

Kenia Startschuss Standard Gauge Railway
ምስል Simon Maina/AFP

ሙሉ ጥንቅሩን ከድምጽ ማዕቀፉ ያድምጡ

እንዳልካቸው ፈቃደ

ማንተጋፍቶት ስለሺ