የአካል ጉዳተኞች የማኅበረሰቡ አካል ናቸዉ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 2 2012« ስለአካል ጉዳተኞች ስናነሳ በተለይ ኢትዮጵያን ሁኔታ ዉስጥ ሲወራ ወይም ሲነሳ አይታይም። የዐቢይ መንግሥት ግን የአካል ጉዳተኞችን ለመርዳት ጥረት ሲያደርግ አይቻለሁ፤ አዉቃለሁ የሚደነቅ ነዉ። በአዲስ አበባም በክፍለሃገርም በግሉም ሲሯሯጥ አይቻለሁ። ስለአካል ጉዳተኞች ስናነሳ፤ በዓለማችን ማነዉ አካል ጉዳኛ፤ ማን ነዉ አካል ጉዳተኛ ያልሆነዉ። በዓለም የጥናት መዘርዝር መሰረት ከዓለም ነዋሪዎች 90 በመቶ አካል ጉዳተኛ ነዉ እንደሚል አቶ ደበበ ሙሉጌታ ይናገራሉ። አቶ ደበበ ሙሉጌታ በታላቋ ብሪታኒያ መኖር ከጀመሩ ብዙ ዓመታትን አስቆጠሩ። በብሪታንያም ቢቢሆን ከአካል ጉዳተኞች ጋር አልያም በአካል ጉዳተኞች ጉዳይ አሁንም መስራታቸዉን አላቆሙም። ኢትዮጵያ ዉስጥም ሳሉ አልፋ መስማት ለተሳናቸዉ የመጀመርያዉ በመንግሥት የሚተዳደር ትምህርት ቤት አስተማሪ እንደነበሩም ይናገራሉ። በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደረገዉን ጥናት በመጥቀስ ከሰዉ ልጅ መካከል 90 በመቶዉ የአካል ጉዳተኛ ነዉ፤ ስለዚህም መከባበር መደጋገፍ መተጋገዝ ይገባናል ይላሉ። አቶ ደበበ እንደሚሉት በዩንቨርስቲ ደረጃ ኢትዮጵያ አብሮነትን የሚያሳዩ ትምርት ቢሰጥም በተግባር ግን የሚታይ ነገር የለም። ባህላችን አቃፊ ቢሆንም ፤ የአካል ጉዳተኞች ግን ይገለላ ሲሉ ይወቅሳሉ። ሌላም አለኝ አሉ በመቀጠል አቶ ደበበ ሙሉጌታ። ማኅበረሰቡ የአካል ጉዳተኞችን የማቀፍ ባህሉን እንዲax,ነክር ግንዛቤዉም እንዲሰፋ ምን መደረግ አለበት ይላሉ? አቶ ደበበ ሙሉጌታ ለሰጡን ቃለ ምልልስ እናመሰግናለን አድማጮች የአካል ጉዳተኞችን በተመለከተ የበለጠ ዉይይት ማድረግን እንሻለን ያላችሁን ጥያቄዎች ብሎም ፤ በዝግጅት ተሳትፎ ማድረግ የሚሻ መልክት አድርሱን በማለt ልሰናበት አዜን ታደሰ ነኝ ጤና ይስጥልኝ።
አዜን ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ