የአውሮጳ ምክር ቤት የምርጫ ውጤት እየፈጠረ ያለው ቀውስ
ሐሙስ፣ ሰኔ 6 2016ባለፈው ሳምንት በ27ቱ የአውሮጳ ኅብረት አገሮች የተካሂደው የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫና ውጤት የአውሮጳ ኅብረትን የወደፊት ቀጣይነት እንዴትነት ብቻ ሳይሆን፤ የአንዳንድ አባል አገሮችን በተለይም የፈረንሳይን ፖለቲካም ያናጋና ቀውስም የፈጠረ ሁኗል።
የአውሮጳ ምክር ቤት ምርጫ ውጤት የመሀል ቀኙ ያውሮጳ ሕዝቦች ፓርቲና የመሀል ግራው የሶሻሊስትና ዲሞክርቶቹ ፓርቲ ከሊበራሎቹና ምናልባትም ከአረንጓዴዎቹ ጋር በመሆን አሁንም በፓርላማው ወሳኞቹ ሀይሎች እንዲሆኑ ዕድል የሰጠ ቢሆንም፤ ከመቼውም ጊዘ ይበልጥ በከፍተኛ ቁጥር ወደ ፓርላማ የመጡት የወግ አጥባቂና የአክራሪ ብሄርተኞች ፓርቲዎች፤ በህብረቱ አሰራሮችና አካሂድ ላይ ጥያቄዎችን በማንሳት እንዲደርደር ለማድረግ የሚይስችል አቅም መገንባታቸው እየትነገረ ነው። ከወዲሁም ወሳኝ የሆነውን የኮሚሽኑንን ፕሪዝደንትና የሌሎቹን ተቁማት መሪዎች በመምረጥ በኩል ፓርቲዎቹ በምርጫው እንዳገኙት ድጋፍ መጠን እየተወያዩና እየተካራከሩ ይገኛሉ።
ወይዘሮ ፎንዴርላየን፤ የኮሚሽኑ ፕሬዝደንት የመሆን ዕድል
ወይዘሮ ኡርሱላ ቮንዴር ለየን ከፍተኛ ድምጽ ያገኘው የአውሮፓ ህዝቦች ፓርቲ ኢፒፒ ቀዳሚ እጩ በመሆናቸውና ከሶሊስቶቹና ሊበራሎቹ ጋር ያለው ጥምረትም ይቀጥላል ተብሎ ስለሚታሰብ፤ በቀጣይም የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት እንደሚሆኑ ይታመናል። ሆኖም ግን፤ ከወግ አጥባቂዎቹ በተለይም ከጣሊያኑ የወይዘሮ ሜሎኒ ፓርቲ ጋር ለመስራት ያሳዩት ፋላጎት የሶሊስቶቹን ድጋፍ ሊያሳጣቸው እንደሚችል የአውሮፕ ሶሊስቶችና ዴሞክራቶች ፓርቲ ዋና ጸሀፊ ሚስተር ጊያኮሞ ፊሊቤክ ሲናገሩ ተሰምተዋል፤ " በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በህብረቱ አጀንድዎችና ፕሮግርሞች ላይ በሚደረገው ድርድር የወግ አጥባቂውና የማንነትና ደሞክራሲ ፓርቲዎች ቁልፍ ሚና እንዲኖራቸው የሚፈቀድ ከሆነ፤ ቀድመን ከድርድሩ የምንወጣው እኛ ነን በማለት ለወይዘሮ ቮንዴርልየን ምርጫው የሳቸው መሆኑን ዐሳውቀዋል።
የምርጫው ውጤት በፈረንሳይ ፖለቲካ ያስክተለው ቀውስ
የአውሮጳ ምክር ቤት ምርጫ ውጤት ክብራስልስ አልፎ በሌሎች አገሮች የውስጥ ፖለቲካ ላይ ከፍተኛ ተጽኖ ሲያሳድር የታየው ዘንድሮ በፈረንሳይ ነው። ፕሬዝዳንት ማክሮን ፓርቲያቸው በአክራሪ ብሄረተኛዋ ማሪ ሌፔን ፓርቲ በእጥፍ ሲበለጥ ፓርላማቸውን በትነው በሶስት ሳምንት ውስጥ ምርጫ እንዲደረግ ማዘዛቸው፤ ብዙዎችን አስደንግጧል አስገርሟልም።፡ማክሮን ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለምን ከዚህ ውሳኔ እንደደረሱ በማብራራት ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎችም በእነዚህ አክራሪ ሀሎች አንጻር በጋራ እንዲሰለፉ ጥሪ አቅርበዋል፤ " የሶሽል ዴሞክራቶቹ፤ አረንጉዴዎቹ፤ ክርስቲያን ዴሞክራቶቹና ሌሎችም ከነዚህ ቡድኖች ጋር መስራት የማይፈልጉ ሀይሎች በነሱ ላይ ግምባር እንደሚፈጥሩ አምናለሁ በማለ፤ ህዝቡም እነዚህ ቡድኖች በኢኮኖሚ፣ በደህንነትና ሌሎች ውሳኝ አጀንዳዎች ላይ ችግር ከመፍጠር በስተቀር የመፍሄ ሀሳብ የሌላቸው መሆኑን በመገንዘብ ድምጹን እንዲነሳቸው ጥሪ አቅርበዋል።፡
የመሀል ቀኙ የፈረንሳይ ሪፑብሊክ ፓርቲ መሪ ሚስተር ኤሪክ ሺዮቲክ ማክሰኞ ዕለት ከወይዘሮ ሌፔን ፓርቲ ጋር እንደሚሰሩ ገልጸው የነበረ ቢሆንም፤ የፓርቲው አባሎች ውሳኒያቸውን ተቃውመው ከመሪነትም እንዳወረዷቸው ተገልጿል፤ ምንም እንኳ ሚስተር ኤሪክ የፓሪውን ቢሮ ቁልፍ ይዘው አሁንም መሪው እኔ ነኝ በማለት እየተክራከሩ መሆኑ ቢነገርም።
ማክሮን ምርጫ እንዲደረግ የፈለጉበት ምክኒያትና ተጠባቂው ውጤት?
ፕሬዝዳንት ማክሮ ፓርቲያቸው በተሸነፈበትና ለአክርሪ ብሄረተኞች የሚስጠው ድጋፍ ከፍተኛ በሆነበት የፖለቲካ ድባብ ምርጫ እንዲደረግ መወሰናቸው ብዙዎች ምን ታይቷቸው ነው በማለት እንዲጠይቁ አድርጉቸዋል ። ጆ ትውይማን የተባሉ የፖለቲክ ተንታኝና ጸህፊ በብኩላቸው ሚስተር ማክሮ ይህን ውሳኔ የወሰኑበትን ምክኒያትና ሊኖረው የሚችለውንም አደጋ ወይም ሪስክ ይጠቅሳሉ፤ " ህዝቡን በማስተበበርና ከጎናቸው በማሰለፍ የቀኝ አክራሪ ሀሎችን ለመታገል ያዋጣል ብለው የወሰዱት እርምጃ ይመስለኛል በማለት ትልቅ ጸረ አክርሪሪ ብሄረተኖች ግምባር በመፍጠር ውጤማ የመሆን ተስፋ ቢኖርም እርግጠና መሆን ግን እንደማይቻል ተናግረዋል የፖለቲካ ተንታኙ።
ሌሎችም የስፔኑን ጠቅላይ ሚኒስተር ፔድሮ ሳንቼዝንና የቀድሞውን የብርታኒያ ጠቅላይ ሚኒስተር ዴዴቪድ ክሜሩንን ውሳኔዎችን፤ ድልና ውድቀቶችን በማንሳትና በማነጻጸር የፕሬዝዳንት ማክሮን እድልም ከህለቱ አንዱ ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስተር ሳንቼዝ በቅርቡ በአካባቢ ምርጫ ሲሸነፉ አጠቃላይ ምርጫ በመጥራት በስልጣን የቆዩ ሲሆን፤ ዴቪድ ካሜሩን ደግሞ ካምስት አመት በፊት የጠሩት ሕዝበ ውሳኔ አገራቸውን ከኅብረቱ እሳቸውንም ከስልጣን ማሰወጣቱ የሚታወስ ነው።
ገበያው ንጉሤ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሠ