1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ኅብረት ምክር ቤታዊ ምርጫ ዉጤት

ሰኞ፣ ግንቦት 18 2006

ትናንት በተጠናቀቀው የአውሮጳ ኅብረት ምክር ቤታዊ ምርጫ ላይ በብዙዎቹ አባል ሀገራት የኅብረቱን አሰራር የሚጠራጠሩት እና የቀኝ ዘመም ፓርቲዎች እንደቀናቸው ተገለጸ።

https://p.dw.com/p/1C7CX
SPD Martin Schulz Empfang in Berlin 25.05.2014
ምስል Reuters

ወግ አጥባቂዎቹ የአውሮጳ ፓርቲዎች ህብረት በምርጫው ፣ ምንም እንኳን የመራጭ ድምፅ ቢያጣም፣ ጠንካራ ቡድን ሆኖዋል። በ28 አባል ሀገራት ውስጥ መጀመሪያ ላይ የወጡ ውጤቶች እንዳሳዩት ይኸው የቀድሞው የሉግዘምቡርግ ጠቅላይ ሚንስትር ዦን ክሎድ ዩንከርን ዋና ዕጩ ያደረገው የወግ አጥባቂዎቹ የአውሮጳ ፓርቲዎች ኅብረት 28% የመራጩን ድምፅ አግኝቶዋል። ጀርመናዊውን ማርቲን ሹልስን ዕጩ ያደረገው የአውሮጳውያኑ ሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲዎች ህብረት ደግሞ 25% አግኝቶዋል። ለዘብተኞቹ ዘጠኝ ከመቶ የመራጩን ድምፅ በማግኘት ሦስተኛውን ቦታ፣ አረንጓዴዎቹ ፓርቲዎች ም ሰባት ከመቶ በማግኘት አራተኛነቱን ቦታ ይዘዋል። በፈረንሳይ በማሪ ለ ፔን የሚመራው የቀኝ አክራሪው «ፍሮ ናስዮናል» 25% የመራጭ ድምፅ፣ በብሪታንያም በኒገል ፋራግ የሚመራው የቀኝ አክራሪው ፓርቲ፣ «ዩኪፕ» 28% በማግኘት በአገሮቻቸው ጠንካራ ፓርቲ ሆነዋል። በዴንማርክ እና በኦስትርያም ቢሆን የቀኝ አክራሪዎቹ ተጨማሪ ድምፅ ሊያገኙ ችለዋል። በግሪክ የኅብረቱን አሰራር የሚጠራጠሩት ፓርቲዎች የፈጠሩት የግራ ህብረት ከ26% በላይ፣ በኢጣልያ ደግሞ 21% የመራጩን ድምፅ አግኝተዋል።
ጀርመንን ጨምሮ የአውሮጳ ኅብረት 28 አባል ሀገራት፤ ካለፈዉ ሐሙስ አንስቶ የጀመሩት የምክር ቤት ምርጫ ትናንት ምሽት ተጠናቋል። አባል ሀገራቱ በጠቅላላ ከሚኖረው ወደ 400 ሚሊዮን ከሚጠጋው ህዝብ ለምርጫ ብቁ የሆኑት አደባባይ ወጥተው ድምጽ እንዲሰጡ ጥሪ ሲቀርብላቸው ነበረ የሰነበተው። ትናንት ምሽት ይፋ በሆነዉ ዉጤት መሰረት አሁንም የመሃል፤ ግራና ለዘብተኛ ፓርቲዎች አብላጫ ድምፅ በማግኘት ምርጫዉ የተጠናቀቀ ቢሆንም፤ የኅብረቱን ፖሊሲ የሚቃወሙና በኅብረቱ ጥርጣሪ ያላቸዉ አክራሪ የግራና ቀኝ ኃይሎች ግን ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት ለመጀመርያ ግዜ ምክር ቤቱን ለመቀላቀል በቅተዋል። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ከዝያዉ የአዉሮጳ ምክር ቤት ከሚገኝበት ከብረስልስ ዘገባ አድርሶናል
ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ

Infografik Europawahl 2014 Sitzverteilung vorl. amtliches Endergebnis ENG
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ