1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 8 2015

የአዉሮጳ ኅብረት በአስገራሚ ሁኔታ እየተባባሰ የመጣውን የኃይል እርምጃ እና በሰው ህይወት ላይ የሚደርሰው ጉዳት እንዳሳሰበው ሰኞ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት በሉክዘምበርግ ባካሂዱት ስብሰባ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታም አንዱ የውይይታቸው ርዕስ ነበር።

https://p.dw.com/p/4IM0X
Äthiopien Tigray Shire | eritreisches Flüchtlingslager
ምስል Joerg Boethling/IMAGO

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሰኞ ዕለት በሉክዘምበርግ ባካሂዱት ስብሰባ ለዩክሬን የሚሰጡትን ወታደራዊ ድጋፍ አጠናክረው ለመቀጠልና በኢራን፤ ተቃውሞ ባሰሙ ሰላማዊ ሰልፈኞች  የሀይል እርምጃ በወሰዱ ባለስልጣኖች ላይ የማዕቀብ እርምጃዎችን ለመውሰድ ወስነዋል።  ሚኒስትሮቹ፤  ህብረቱ ከቻይና ጋር ያለውን ግንኙኑነት በሚመለክትም ቻይና ባላንጣም አጋርም መሆኗን በመገንዘብ ህብረቱ ግንንኙነቱን ጥቅሙን በሚያስጠብቅና በሚያረጋግጥ ሁኔታ በጥንቃቄ እንዲቀጥል የተስማሙ መሆኑ ተገልጿል።  በኢትዮጵያ ላይ ባደረጉት ውይይትም  የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ባስቸኳይ የሰላም ንግግር እንዲጀምሩ ጥሪ ያስተላለፉ መሆኑ ታውቋል።  

ሩሲያ በዩክሬን እያካሄደችው ባለው ጦርነት፤ የውሮፓ ህብረትና አባል አገሮቹ ወታደሮችን በዩክሬን ከማዝመት በመለስ በከፍተኛ ደረጃ እየተሳተፉና ዋጋም እየከፈሉ መሆኑ የሚታወቅ ነው። በቅርቡ ፕሬዝዳንት ፑቲን አራት የዩክሬን ግዛቶችን ወደ ሩሲያ እንዲጠቃለሉ መወናሰቸው ደግሞ፤ የአውሮፓ ህብረትና አባል አገሮቹን ከሩሲያ ጋር ይበልጥ ቅራኔ ውስጥ ከቷቸዋል፤ ወታደራዊ ፍጥጫም ፈጥሯል። በዚህም ምክኒያት ዛሬ በአውሮፓ በሁሉም ቦታ ዋናው አጀንዳ የዩክሬን - ሩሲያ ጦርነት ሲሆን፤ የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሀላፊና የስብሰባው መሪ ሚስትር ጆሴፕ ቦርየል እንደገለጹት ዛሬ የአውሮፓ ቅድሚያ ግዴታ ከዩክሬን ጎን መቆም ነው።  

ጆሴፕ ቦሬል
የአውሮጳ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሀላፊና የስብሰባው መሪ ጆሴፕ ቦሬልምስል Lenoir/EUC/ROPI/picture alliance

ሚስተር ቦርየል የስብሰባውን ውጤትና ውሳኔዎችን ባስታወቁበት ጋዜጣዊ መግለጫቸው፤ህብረቱ በዚህ ጦርነት፤ ለዩክሬን ሁለንተናዊ ድጋፍ በመስጠት፤ በሩሲያ ላይ ጫና በመፍጠርና ጦርነቱ ያስከተላቸውን ዘርፍ ብዙ ችግሮች በመቋቋም በሶስት ዘርፎች የሚያደርገውን ተሳትፎ አስታውሰው፤ ሚኒስትሮቹ በዚህ ስብሰባቸው ሁለት ተጨባጭ እርምጃዎችን የወሰዱ መሆኑን አስታውቀዋል፤ “ “አንደኛ  ለዩክሬን ሰራዊት ስልጠናና ድጋፍ የሚሰጥ  ወታደራዊ ሚሽን እንዲቋቋም  ወስነናል። ይህ ሚሺን የሚመሰረተው በዩክሬን ውስጥ ሳይሆን በህብረቱ አባል አገር ነው፤ አላማውም የዩክሬንን ወታደሮች ማሰልጠን ሲሆን፤ ባስቸኳይም 15 ሺ ወታደሮችን የሚያሰለጥን ይሆናል።  

ሁለተተኛ ለዩክሬን ወታደራዊ ድጋፍ ተጨማሪ 500 ኢሮ ለመስጠት ወሰነናል” በማለት ህብረቱ እስካሁን ለዩክሬን ወታደራዊ እርዳታ 3.1 ቢሊዮን ኢሮ የሰጠ መሆኑና ወደፊትም እርዳታው እንደሚቀጥል ገልጸዋል።  

ሚስተር ቦርዬል ኢትዮጵያን በሚመለክት ሚኒስትሮቹ፤ ጦረነት የፖለቲካ ችግር መፍቻ መሳሪያ ሊሆን  እንደማይችል በማስታወስ፤ ሁሉም ወገኖች ጦርነቱን አቁመው ለውይይትና ድርድር እኒዲቀመጡ ጥሪ ያቀረቡ መሆኑን አስታውቀዋል። ይህንን የሚኒስትሮቹን ውሳኔና የሰላም ጥሪ ሚስተር ቦርየል በጋዜጣዊ መገለጫቸው አጽናኦት ስተውታል። “ጦርነቱ ባስቸኳይ እንዲቆም፣ የኤርትራ ሀይሎች ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጡ፣ የሰባዊ እርዳታ ባስቸኳይና ያለገደብ ወደ ትግራይ እንዲደርስ እንዲደረግ፣ የሰባዊ መብቶችንና የዓለማቀፍ ህጎችን በጣሱ ሀይሎች ላይ ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጥሪያችንን እናስተላለፋለን በማለት፤ የኢትዮጵያ መንግስትና የትግራይ ሀይሎች የአፍርካ ህብረትን የሰላም ጥሪ ተግባራዊ በማድረግ የሰላም ንግግሩን እንዲጀምሩ ሚኒስትሮቹ ጥሪ ያስተላለፉ መሆኑን ሚስተር ቦርየል አስታውቀዋል።   

ሁለት አመት ሊሞላው ቀናት የቀሩት የፌደራል መንግስቱና የህወሀት ጦርነት በተለይ ሰሞኑን በሽሬ አካባቢ ከደረሰ ውዲህ፤ የመንግስታቱ ድርጅት፤ የአሜሪካና ሌሎች መንግስታት ጦርነቱ እንዲቆምና የሰላም ንግግር እንዲጀመር በየግላቸው ጥሪ እያስተላለፉ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤. ሚስተር ቦርየልም በትናንትናው ዕለት ይህንኑ የሚኒስትሮቹን ማሳሰቢያና ጥሪ የሚደግም መግለጫ በህብረቱ ስም አውተዋል። 

ገበያው ንጉሤ
ልደት አበበ
ኂሩት መለሰ