1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፄ ኃይለ ስላሴ 35ኛ ሙት ዓመትና ዝካሬ

ዓርብ፣ ነሐሴ 21 2002

የመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉስ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ የመሞታቸውን መርዶ በወቅቱ ስልጣን ጨብጦ በነበረው ደርግ ይፋ የተደረገው ከ35 በፊት በዛሬዋ ዕለት ነበር ።

https://p.dw.com/p/Oy7d
ንጉስ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴምስል AP

የአፄ ኃይለ ስላሴ አሟሟት እስከ ዛሬ ድረስ እንቅልልሽ ነው። በዕርጅናም ሆነ በህመም ሳቢያ መሞታቸው ወይም በሰው እጅ ህይወታቸው ማለፉ እስካሁን ግልፅ አይደለም። 44 ዓመት ኢትዮጵያን በንጉሰ ነገስትነት ያስተዳደሩት አፄ ኃይለ ስላሴ በውጭው ዓለም እጅግ የሚከበሩ ታላቅ የሀገር መሪ እንደነበሩ እስካሁን ድረስ ይመሰከርላቸዋል። በተለያዩ ሀገሮች ጉብኝት ሲያደርጉ የሚያጋጥማቸው አቀባበል እጅግ ደማቅና ክብር የተሞለበት ነበር ።፡ ለኝህ ንጉስ ታላቅ አክብሮት ካላቸው አገሮች አንዷ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኃላ ስትቋቋም የጎበኙዋት ምዕራብ ጀርመን ናት። ለርሳቸው ይሰጥ ከነበረ ታላቅ አክብሮትና ፅኑ ወዳጅነት በመነሳት ዛሬም ቢሆን የጀርመን መገናኛ ብዙሀን ወደ ታሪክ አምድ መለስ ብለው አዘክረዋቸዋል። ይልማ ኃይለ ሚካኤል ዘገባ አለዉ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል፣ አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ